-
‘ሥቃያቸውን ተረድቼአለሁ’መጠበቂያ ግንብ—2009 | መጋቢት 1
-
-
በአንድ ወቅት ሙሴ በጎች እየጠበቀ ሳለ አንድ አስገራሚ ነገር ተመለከተ፤ በአቅራቢያው የነበረ አንድ ቍጥቋጦ በእሳት ቢያያዝም ‘አልተቃጠለም’ ነበር። (ቁጥር 2) ሙሴ በሁኔታው በጣም ስለተገረመ ነገሩን ለማጣራት ወደ ቁጥቋጦው ተጠጋ። በዚህ ጊዜ ይሖዋ በአንድ መልአክ አማካኝነት በእሳቱ መካከል ተገልጦ ሙሴን “ወደዚህ እንዳትቀርብ፤ ይህች የቆምኽባት ምድር የተቀደሰች ስለሆነች ጫማህን አውልቅ” አለው። (ቁጥር 5) የሚነደው ቁጥቋጦ የአምላክን መገኘት ይወክል ስለነበር መሬቱ እንኳ ሳይቀር ቅዱስ ሆኖ ነበር!
-
-
‘ሥቃያቸውን ተረድቼአለሁ’መጠበቂያ ግንብ—2009 | መጋቢት 1
-
-
አምላክ ሩኅሩኅ መሆኑ ተስፋ እንዲኖረን ያደርጋል። ፍጽምና የጎደለን ብንሆንም በእሱ እርዳታ በተወሰነ ደረጃ ቅዱስ መሆን የምንችል ከመሆኑም ሌላ በእሱ ፊት ተቀባይነት ያለው አቋም ይዘን መገኘት እንችላለን። (1 ጴጥሮስ 1:15, 16) በመንፈስ ጭንቀትና በተስፋ መቁረጥ ስሜት ትሠቃይ የነበረች አንዲት ክርስቲያን፣ ሙሴ ከቁጥቋጦው ጋር በተያያዘ ስላጋጠመው ሁኔታ የሚናገረው ዘገባ አጽናንቷታል። እንዲህ በማለት ገልጻለች፦ “ይሖዋ መሬቱን እንኳ ቅዱስ ማድረግ ከቻለ እኔም የተስፋ ጭላንጭል ሊኖረኝ ይችላል። እንዲህ ዓይነት አመለካከት መያዜ በእጅጉ ረድቶኛል።”
-