የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—መስከረም 2020
    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—2020 | መስከረም
    • አሮን ስህተት በሠራባቸው በሦስቱም ጊዜያት የመጥፎ ድርጊቱ ዋነኛ ጠንሳሽ ተደርጎ አለመገለጹ ትኩረት የሚስብ ነው፤ ከዚህ ይልቅ ከትክክለኛው ጎዳና የራቀው በሁኔታዎች ወይም በሌሎች ሰዎች ተጽዕኖ ተሸንፎ ሳይሆን አይቀርም። በተለይ መጀመሪያ ጊዜ ስህተት በሠራበት ወቅት “ብዙኃኑን ተከትለህ ክፉ ነገር አታድርግ” ከሚለው ትእዛዝ በስተ ጀርባ ያለውን መሠረታዊ ሥርዓት በሥራ ላይ ማዋል ይችል ነበር። (ዘፀ 23:2) ያም ቢሆን ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ከዚያ በኋላ የአሮን ስም የተነሳው በመልካም ነው፤ የአምላክ ልጅም ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ከአሮን ዘር የመጣው ክህነት ሕጋዊ መሆኑን ገልጿል።—መዝ 115:10, 12፤ 118:3፤ 133:1, 2፤ 135:19፤ ማቴ 5:17-19፤ 8:4

  • የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—መስከረም 2020
    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—2020 | መስከረም
    • ከፍርድ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ፍትሕን ማጣመም በመታወር ተመስሏል፤ ሕጉ ጉቦን፣ ስጦታን ወይም አድልዎን አስመልክቶ በርካታ ማስጠንቀቂያዎችን ይዟል፤ ምክንያቱም እንዲህ ያሉት ነገሮች አንድ ዳኛ እንዲታወርና ፍትሐዊ የሆነ ፍርድ እንዳያስተላልፍ ሊያደርጉት ይችላሉ። “ጉቦ አጥርተው የሚያዩ ሰዎችን ዓይን ያሳውራል።” (ዘፀ 23:8) “ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራል።” (ዘዳ 16:19) አንድ ዳኛ ምንም ያህል ጻድቅና አስተዋይ ቢሆንም እንኳ ከባለጉዳዮቹ የሚሰጠው ስጦታ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተጽዕኖ ሊያሳድርበት ይችላል። የአምላክ ቃል አንድ ሰው ስጦታ ብቻ ሳይሆን የገዛ ስሜቱም ሊያሳውረው እንደሚችል ይገልጻል፤ እንዲህ ይላል፦ “ለድሃው አታዳላ ወይም ባለጸጋውን ከሌሎች አስበልጠህ አትመልከት።” (ዘሌ 19:15) በመሆኑም አንድ ዳኛ በስሜት ተገፋፍቶ ወይም የብዙኃኑን ተወዳጅነት ለማግኘት በማሰብ በሀብታሞች ላይ ሀብታም በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሊፈርድባቸው አይገባም።—ዘፀ 23:2, 3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ