የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የይሖዋን አስተሳሰብ ያወቀ ማን ነው?”
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥቅምት 15
    • 14. ሙሴ ይሖዋ ለተናገረው ሐሳብ ምን ምላሽ ሰጠ?

      14 ዘገባው ቀጥሎ እንዲህ ይላል፦ “ሙሴ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቸርነት ፈለገ፤ እንዲህም አለ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ በታላቅ ሥልጣንህና በኀያል ክንድህ ከግብፅ ባወጣኸው ሕዝብህ ላይ ቍጣህ ለምን ይነዳል? ግብፃውያን፣ “በተራራዎቹ ላይ ሊገድላቸው ከገጸ ምድርም ሊያጠፋቸው ስለ ፈለገ ነው ያወጣቸው” ለምን ይበሉ? ከክፉ ቍጣህ ተመለስ፤ ታገሥ፤ በሕዝብህም ላይ ጥፋት አታምጣ። ለባሪያዎችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለእስራኤል፣ “ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ለዘርህም ተስፋ አድርጌ የሰጠኋቸውን ይህችን ምድር ሁሉ እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘላለምም ርስታቸው ትሆናለች” በማለት በራስህ የማልኸውን አስታውስ።’ ከዚያም እግዚአብሔር ታገሠ፤ በሕዝቡም ላይ አመጣባቸዋለሁ ያለውን ጥፋት አላመጣባቸውም።”—ዘፀ. 32:11-14a

  • “የይሖዋን አስተሳሰብ ያወቀ ማን ነው?”
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥቅምት 15
    • 16 ሙሴ የሰጠው ምላሽ ይሖዋ ፍትሐዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያለውን እምነት ያሳያል። በተጨማሪም የሰጠው ምላሽ የራሱን ጥቅም ከማስቀደም ይልቅ ለይሖዋ ስም እንደሚቆረቆር የሚያሳይ ነበር። የይሖዋ ስም እንዲነቀፍ አልፈለገም። ሙሴ ይህን ማድረጉ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ “የይሖዋን አስተሳሰብ” እንዳወቀ የሚያሳይ ነው። (1 ቆሮ. 2:16) ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ? በመንፈስ መሪነት ከተጻፈው ዘገባ መገንዘብ እንደሚቻለው ይሖዋ የተወሰነ እርምጃ ለመውሰድ ቁርጥ ውሳኔ ስላላደረገ “በሕዝቡም ላይ አመጣባቸዋለሁ ያለውን ጥፋት አላመጣባቸውም።” ይሖዋ በመላው ብሔር ላይ ሊወስድ የፈለገውን እርምጃ አልወሰደም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ