የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ባሕርያቱን ሲገልጽ
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ግንቦት 1
    • ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ሳለ ይሖዋን “እባክህ፤ ክብርህን አሳየኝ” በማለት ለምኖት ነበር። (ዘፀአት 33:18) በማግሥቱ ይህ ነቢይ የአምላክን ክብር ለቅጽበት የመመልከት መብት አገኘ።a ሙሴ በዚያ ወቅት ስለተመለከተው አስደናቂ ራእይ በዝርዝር አልጻፈም። ሆኖም ከዚያ ይበልጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ነገር ይኸውም አምላክ የተናገረውን ሐሳብ በጽሑፍ አስፍሮልናል። እስቲ በዘፀአት 34:6, 7 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ይሖዋ የተናገረውን ሐሳብ እንመርምር።

      ይሖዋ ስለ ራሱ የገለጠው የመጀመሪያው ነገር “መሐሪና ቸር የሆነ አምላክ” መሆኑን ነው። (ቁጥር 6 NW) አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑር እንደገለጹት “መሐሪ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል አምላክ “አባት ለልጆቹ የሚያሳየው ዓይነት ከአንጀት የመነጨ ርኅራኄ” እንዳለው የሚጠቁም ነው። “ቸር” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ደግሞ “አንድ ሰው ችግር ላይ የወደቀ ግለሰብን ለመርዳት ሲል ከልቡ ተነሳስቶ የሚወስደውን እርምጃ” ከሚገልጽ ግስ ጋር ተዛማጅነት አለው። ከዚህ በግልጽ ለመመልከት እንደምንችለው ይሖዋ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን በሚይዙበት መንገድ እሱም አገልጋዮቹን እንደሚንከባከባቸው እንድናውቅ ይፈልጋል። ወላጆች ለልጆቻቸው ጥልቅ ፍቅር እንዳላቸውና ልባዊ አሳቢነት እንደሚያሳዩአቸው ሁሉ ይሖዋም አምላኪዎቹን በዚህ መንገድ ይንከባከባቸዋል።—መዝሙር 103:8, 13

      በመቀጠልም ይሖዋ “ለቍጣ የዘገየ” መሆኑን ገልጿል። (ቁጥር 6) በምድር ባሉ አገልጋዮቹ ላይ በቀላሉ አይቆጣም። ይልቁንም ከኃጢአት ጎዳናቸው እንዲመለሱ ጊዜ በመስጠት ድክመታቸውን ይታገሣል።—2 ጴጥሮስ 3:9

      አምላክ “ፍቅራዊ ደግነቱና እውነቱ እጅግ የበዛ” መሆኑንም ገልጿል። (ቁጥር 6 NW) ፍቅራዊ ደግነት ወይም ታማኝ ፍቅር፣ በይሖዋና በሕዝቦቹ መካከል የጸና እንዲሁም ምንጊዜም የማይለወጥ ትስስር እንዲፈጠር የሚያደርግ ግሩም ባሕርይ ነው። (ዘዳግም 7:9) ከዚህም በላይ ይሖዋ የእውነት ምንጭ ነው። ይሖዋ አያታልልም፤ በሌሎችም አይታለልም። “የእውነት አምላክ” ስለሆነ ስለወደፊቱ ጊዜ የሰጣቸውን ተስፋዎች ጨምሮ የተናገራቸውን ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጽም ሙሉ በሙሉ ልንተማመን እንችላለን።—መዝሙር 31:5

  • ይሖዋ ባሕርያቱን ሲገልጽ
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ግንቦት 1
    • a ማንም ሰው አምላክን አይቶ በሕይወት መኖር ስለማይችል ሙሴ ይሖዋን ቃል በቃል አልተመለከተውም። (ዘፀአት 33:20) ከሁኔታዎቹ መረዳት እንደሚቻለው ይሖዋ ለሙሴ በራእይ ክብሩን ያሳየው ሲሆን በመልአክ አማካኝነት አነጋግሮታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ