የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ—ከሁሉ የላቀው የጥሩነት ምሳሌ
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ጥር 15
    • 12 በሚቀጥለው ቀን በሲና ተራራ ላይ የይሖዋ ጥሩነት በሙሴ ፊት አለፈ። በዚህ ወቅት ሙሴ የአምላክን ክብር በመጠኑ የተመለከተ ሲሆን የሚከተለውን መግለጫም ሰምቷል:- “ይሖዋ፣ ይሖዋ መሐሪ፣ ደግ፣ ለቁጣ የዘገየ፣ ፍቅራዊ ደግነቱና እውነቱ የበዛ፣ እስከ ሺህ ትውልድም ፍቅራዊ ደግነትን የሚጠብቅ፣ ስህተትና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፣ [በደለኛውን] ሳይቀጣ የማያልፍ፣ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆችና በልጅ ልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ የሚያመጣ አምላክ ነው።” (ዘጸአት 34:6, 7 NW ) እነዚህ ቃላት የይሖዋ ጥሩነት ከፍቅራዊ ደግነቱና ሌሎች ባሕርያቱ ጋር የተዛመደ መሆኑን ይጠቁማሉ። እነዚህን ባሕርያት መመርመራችን የጥሩነትን ባሕርይ ለማንጸባረቅ ይረዳናል። በመጀመሪያ ስለ አምላክ ጥሩነት በተነገረው በዚህ አስገራሚ መግለጫ ውስጥ ሁለት ጊዜ የተጠቀሰውን ባሕርይ እንመልከት።

  • ይሖዋ—ከሁሉ የላቀው የጥሩነት ምሳሌ
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ጥር 15
    • 13. ስለ አምላክ ጥሩነት በተሰጠው መግለጫ ውስጥ ሁለት ጊዜ የተጠቀሰው ባሕርይ የትኛው ነው? ይህስ ተስማሚ የሆነው ለምንድን ነው?

      13 “ይሖዋ . . . ፍቅራዊ ደግነቱ . . . የበዛ . . . እስከ ሺህ ትውልድም ፍቅራዊ ደግነትን የሚጠብቅ . . . አምላክ ነው።” “ፍቅራዊ ደግነት” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል “ታማኝ ፍቅር” የሚል ትርጉምም አለው። አምላክ ለሙሴ በሰጠው መግለጫ ውስጥ ሁለት ጊዜ ተጠቅሶ የሚገኘው ብቸኛ ባሕርይ ይህ ነው። የይሖዋ ዋነኛ ባሕርይ ፍቅር ከመሆኑ አንጻር ይህ ምንኛ ተስማሚ ነው! (1 ዮሐንስ 4:​8) “ጥሩ ነውና፤ ፍቅራዊ ደግነቱም ለዘላለም ነውና” የሚለው ለይሖዋ የሚቀርበው በሰፊው የታወቀ የውዳሴ መግለጫ ይህንን ባሕርይ ጎላ አድርጎ የሚገልጽ ነው።

  • ይሖዋ—ከሁሉ የላቀው የጥሩነት ምሳሌ
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ጥር 15
    • 19. ይሖዋ ንስሐ ለሚገቡ ኃጢአተኞች ምን ድንቅ ጥሩነት አሳይቷል?

      19 “ይሖዋ . . . ስህተትና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል . . . አምላክ ነው።” ይሖዋ በጥሩነቱ የተነሳ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር ለማለት ዝግጁ ነው። አፍቃሪ የሆነው ሰማያዊ አባታችን በኢየሱስ መሥዋዕት አማካኝነት ይቅርታ ማግኘት የምንችልበትን ዝግጅት በማድረጉ በጣም አመስጋኝ ነን። (1 ዮሐንስ 2:​1, 2) በቤዛው ላይ እምነት ያላቸው ሁሉ ቃል በተገባው አዲስ ዓለም ውስጥ ፍጻሜ የሌለው ሕይወት የማግኘት ተስፋ መጨበጣቸውና በይሖዋ ፊት ሞገስ አግኝተው ከእርሱ ጋር መወዳጀት መቻላቸው ያስደስተናል። ለሰው ልጅ ያሳየው ይህ ጥሩነት ይሖዋን የምናወድስበት እንዴት ያለ ግሩም ምክንያት ነው!​—⁠2 ጴጥሮስ 3:​13

      20. አምላክ የክፋት ድርጊትን አቅልሎ እንደማይመለከት ምን ማረጋገጫ አለን?

      20 “ይሖዋ . . . ሳይቀጣ የማያልፍ፣ . . . አምላክ ነው።” ይህም ቢሆን ይሖዋን ስለ ጥሩነቱ እንድናወድሰው የሚያደርግ ሌላ ምክንያት ነው። ለምን? ምክንያቱም የጥሩነት አንዱ መሠረታዊ ገጽታ በምንም ዓይነት መንገድ ክፉ ድርጊትን አቃልሎ አለመመልከቱ ነው። ከዚህም በተጨማሪ “ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር . . . ሲገለጥ . . . እግዚአብሔርን የማያውቁትን፣ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል።” ‘በዘላለምም ጥፋት ይቀጣሉ።’ (2 ተሰሎንቄ 1:6-9) ከዚያ በኋላ በሕይወት የሚተርፉት የይሖዋ አምላኪዎች ‘ጥሩ የሆነውን በማይወዱ’ አምላካዊ አክብሮት የሌላቸው ሰዎች ሳይታወኩ ሕይወትን ያጣጥሟታል።​—⁠2 ጢሞቴዎስ 3:​1-3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ