-
ምንጊዜም ጥሩነት አሳዩመጠበቂያ ግንብ—2002 | ጥር 15
-
-
10. በዘጸአት 34:6, 7 NW ላይ የተጠቀሱት የይሖዋ ጥሩነት ገጽታዎች ምንድን ናቸው?
10 ከአምላክ ቃል በምናገኘው መንፈሳዊ ብርሃንና በአምላክ ቅዱስ መንፈስ እርዳታ ‘ጥሩ የሆነውን ማድረጋችንን መቀጠል’ እንችላለን። (ሮሜ 13:3 NW ) አዘውትረን መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና የይሖዋን ጥሩነት መምሰል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይበልጥ እየተማርን እንሄዳለን። ከዚህ በፊት የነበረው ርዕስ በዘጸአት 34:6, 7 NW ላይ ተመዝግቦ በሚገኘውና ሙሴ በሰማው መግለጫ ላይ የተጠቀሱትን የአምላክ ጥሩነት አንዳንድ ገጽታዎች አብራርቷል። ጥቅሱ እንዲህ ይነበባል:- “ይሖዋ፣ ይሖዋ መሐሪ፣ ደግ፣ ለቁጣ የዘገየ፣ ፍቅራዊ ደግነቱና እውነቱ የበዛ፣ እስከ ሺህ ትውልድም ፍቅራዊ ደግነትን የሚጠብቅ፣ ስህተትና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፣ [በደለኛውን] ሳይቀጣ የማያልፍ . . . አምላክ ነው።” ይህንን የይሖዋ ጥሩነት መግለጫ በጥልቀት መመርመራችን ‘ጥሩ የሆነውን ማድረጋችንን እንድንቀጥል’ ይረዳናል።
-
-
ምንጊዜም ጥሩነት አሳዩመጠበቂያ ግንብ—2002 | ጥር 15
-
-
14. ይቅር ባይ መሆን የሚኖርብን ለምንድን ነው?
14 አምላክ ለሙሴ የሰጠው መግለጫ ይቅር ባይ እንድንሆንም ሊያንቀሳቅሰን ይገባል። ምክንያቱም ይሖዋ ራሱ ይቅር ለማለት ዝግጁ ነው። (ማቴዎስ 6:14, 15) እርግጥ ይሖዋ ንስሐ የማይገቡ ኃጢአተኞችን ይቀጣል። በመሆኑም የጉባኤውን መንፈሳዊ ንጽሕና መጠበቅን በተመለከተም የእርሱን የጥሩነት የአቋም ደረጃ ማክበር ይኖርብናል።—ዘሌዋውያን 5:1፤ 1 ቆሮንቶስ 5:11, 12፤ 1 ጢሞቴዎስ 5:22
-