-
“በምትናገርበት ጊዜ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ”የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ—2020 | ሰኔ
-
-
“በምትናገርበት ጊዜ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ”
ሙሴ በይሖዋ እርዳታ ፍርሃቱን ማሸነፍ ችሏል። ይሖዋ ሙሴን ከያዘበት መንገድ ምን ትምህርት እናገኛለን?
ባለብን የአቅም ገደብ ላይ ትኩረት ማድረግ የለብንም
የተሰጠንን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልገንን ማንኛውንም እርዳታ ይሖዋ እንደሚሰጠን መተማመን እንችላለን
ለሰው ፍርሃት ማርከሻው በአምላክ ላይ እምነት ማሳደር ነው
-
-
መስበክና ማስተማር ትችላላችሁ!የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ—2020 | ሰኔ
-
-
መስበክና ማስተማር ትችላላችሁ!
መጀመሪያ ላይ ሙሴ ይሖዋ የሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ብቃቱ እንዳለው አልተሰማውም ነበር። (ዘፀ 4:10, 13) አንተስ እንደዚህ ተሰምቶህ ያውቃል? ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን እያጠናህ ነው? መቼም ቢሆን ከቤት ወደ ቤት መስበክ እንደማትችል ተሰምቶህ ያውቃል? ወይም ትምህርት ቤት ውስጥ መመሥከር የሚከብድህ ወጣት ልትሆን ትችላለህ። አሊያም ደግሞ በስልክ መስበክ ወይም በአንድ ዓይነት የአደባባይ ምሥክርነት ዘርፍ መካፈል ያስፈራህ ይሆናል። ከሆነ ይሖዋ መንፈስ ቅዱስን እንዲሰጥህ በጸሎት ለምነው። (1ጴጥ 4:11) ይሖዋ እሱ የሰጠህን የትኛውንም ኃላፊነት ለመወጣት እንደሚረዳህ መተማመን ትችላለህ።—ዘፀ 4:11, 12
-