የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ይህ ለመታሰቢያ ይሁናችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ታኅሣሥ 15
    • 9. በዘፀአት 12:6 መሠረት የፋሲካው በግ የሚታረደው ስንት ሰዓት ላይ ነው? (በተጨማሪም “ስንት ሰዓት ላይ ነው?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።)

      9 ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር በተዘጋጀው አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ የዘፀአት 12:6 የግርጌ ማስታወሻ፣ በጉ መታረድ ያለበት “በሁለት ምሽት መካከል” እንደሆነ ይናገራል። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በዋናው ጽሑፍ ላይ ይህንን ጥቅስ የተረጎሙትም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ነው። በአንዳንድ የአማርኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ ይህ አገላለጽ “ምሽት ላይ” እና “ጀምበር ስትጠልቅ” ተብሎ ተተርጉሟል። በመሆኑም በጉ የሚታረደው ኒሳን 14 መጀመሪያ ላይ ይኸውም ጀምበር ከጠለቀች በኋላ ሆኖም ሙሉ በሙሉ ከመጨለሙ በፊት ነው።

      10. አንዳንዶች የፋሲካ በግ መታረድ ያለበት መቼ ነው ይላሉ? ይህስ ምን ጥያቄ ያስነሳል?

      10 ከጊዜ በኋላ አንዳንድ አይሁዳውያን፣ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚመጡትን በጎች በሙሉ ለማረድ ብዙ ሰዓት ሊፈጅ እንደሚችል ይሰማቸው ጀመር። በመሆኑም በዘፀአት 12:6 ላይ የተጠቀሰው ወቅት ኒሳን 14 ሊያበቃ ሲል ያለውን ጊዜ ይኸውም ፀሐይ ማዘቅዘቅ ከምትጀምርበት ጊዜ (ከእኩለ ቀን) አንስቶ ጀምበር ጠልቃ ቀኑ እስከሚያበቃበት ድረስ ያለውን ጊዜ እንደሚያመለክት ማሰብ ጀመሩ። ይሁን እንጂ በጎቹ የሚታረዱት ኒሳን 14 ማብቂያ ላይ ከሆነ ፋሲካው የሚበላው መቼ ነው? የጥንት የአይሁድ እምነት ሊቅ የሆኑት ፕሮፌሰር ጆናታን ክላዋንስ እንዲህ ብለዋል፦ “አዲስ ቀን የሚጀምረው ፀሐይ ስትጠልቅ ነው፤ በመሆኑም መሥዋዕቱ የሚቀርበው በ14ኛው ቀን ቢሆንም ፋሲካ የሚጀምረውና የሚበላው በ15ኛው ቀን ነው፤ እርግጥ የዘፀአት መጽሐፍ በዓሉ በዚህ ቀን መከበር እንዳለበት የሚናገረው ነገር የለም።” አክለውም እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦ “የረቢዎች ጽሑፍ ቤተ መቅደሱ [በ70 ዓ.ም.] ከመጥፋቱ በፊት ሴደር [የፋሲካ ምግብ] እንዴት ይበላ እንደነበር እንኳ አይገልጽም።”—በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።

  • ‘ይህ ለመታሰቢያ ይሁናችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ታኅሣሥ 15
    • ስንት ሰዓት ላይ ነው?

      አይሁዳዊ ተንታኝ የሆኑት ማርከስ ካሊሽ (1828-1885) እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦ “ኢብን ዕዝራ [የታወቀ ስፔናዊ ረቢ፣ 1092-1167] በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው አመለካከት ተመሳሳይ ነው፤ ኢብን ዕዝራ እንዲህ ብለዋል፦ ‘ሁለት ምሽቶች አሉን፤ የመጀመሪያው ፀሐይዋ መጥለቅ ስትጀምር ያለው . . . ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሰማዩ ላይ የሚታየው የፀሐይ ነጸብራቅ ሙሉ በሙሉ ሲጠፋ ያለው ነው፤ በሁለቱ ምሽቶች መካከል የአንድ ሰዓት ከሃያ ደቂቃ ገደማ ልዩነት አለ፤’ በተጨማሪም ይህን በጣም ምክንያታዊ የሚመስል ማብራሪያ ቀረዓታውያን፣ ሳምራውያንና ሌሎች በርካታ ሰዎች ተቀብለውታል።” በጉ መታረድ ያለበት ኒሳን 14 ሲጀምር እንደሆነ የሚገልጸው አመለካከት በዘዳግም 16:6 ላይ “ፀሓይ ስትጠልቅ ምሽቱ ላይ ከግብፅ በወጣህበት ሰዓት ዓመታዊ መታሰቢያ (በዚያ) ፋሲካን ሠዋ” ተብሎ ለእስራኤላውያን ከተሰጠው መመሪያ ጋር ይስማማል።—ዘፀ. 30:8፤ ዘኍ. 9:3-5, 11

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ