-
ይሖዋ የአቅማችንን ውስንነት ግምት ውስጥ ያስገባልመጠበቂያ ግንብ—2009 | ሰኔ 1
-
-
ይሁንና ግለሰቡ ሁለት ዋኖሶችን እንኳ ለማቅረብ አቅሙ የማይፈቅድለት ቢሆንስ? በዚህ ጊዜ ሕጉ “የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ [አንድ ኪሎ ግራም ገደማ] የላመ ዱቄት ለኀጢአት መሥዋዕት ያቅርብ” ይላል። (ቁጥር 11) ይሖዋ፣ በጣም ድሃ ለሆኑ ሰዎች ልዩ አስተያየት በማድረግ ደም ሳይፈስ የኃጢአት ይቅርታ እንዲያገኙ ዝግጅት አድርጎላቸዋል።a አንድ እስራኤላዊ የቱንም ያህል ድሃ ቢሆን፣ ይህ ሁኔታው የኃጢአት ይቅርታ እንዳያገኝ እንቅፋት አይሆንበትም፤ ወይም ከአምላክ ጋር ሰላም ለመፍጠር የሚያስችለውን አጋጣሚ አይነፍገውም።
-
-
ይሖዋ የአቅማችንን ውስንነት ግምት ውስጥ ያስገባልመጠበቂያ ግንብ—2009 | ሰኔ 1
-
-
a ለመሥዋዕት የሚቀርብ አንድ እንስሳ፣ ኃጢአት የማስተሰረይ ኃይሉ ያለው አምላክ እንደ ቅዱስ አድርጎ በሚመለከተው በደሙ ላይ ነው። (ዘሌዋውያን 17:11) ታዲያ ይህ ሲባል ድሆች የሚያቀርቡት የዱቄት መሥዋዕት ዋጋ የለውም ማለት ነው? በፍጹም። ይሖዋ፣ አንድ እስራኤላዊ እንዲህ ያለውን መሥዋዕት እንዲያቀርብ ያነሳሳውን የትሕትናና የፈቃደኝነት መንፈስ እንደሚያደንቅ ብሎም ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠው ጥርጥር የለውም። ከዚህም ሌላ ድሆችን ጨምሮ የመላው ብሔር ኃጢአት በዓመታዊው የስርየት ቀን ለአምላክ በሚቀርቡት የእንስሳት ደም ይሸፈን ነበር።—ዘሌዋውያን 16:29, 30
-