የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ልክ እንደ አምላክ ለሕይወት ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለህ?
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
    • 5, 6. የሙሴ ሕግ ደም ቅዱስና ውድ ነገር እንደሆነ የሚያሳየው እንዴት ነው? (በተጨማሪም “ለእንስሳት ሕይወት አክብሮት ይኑርህ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።)

      5 እነዚህ ሁለት መሠረታዊ እውነቶች በሙሴ ሕግ ውስጥ ተንጸባርቀዋል። ዘሌዋውያን 17:10, 11 እንዲህ ይላል:- “ማንኛውም [ሰው] . . . ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ፤ የፍጡር ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ በመሠዊያ ላይ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ደሙን ሰጥቻችኋለሁ፤ ለሰውም ሕይወት ስርየት የሚያስገኝ ደም ነው።”a—“ደም ያለው የማስተሰረይ ኃይል” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።

      ደም ያለው የማስተሰረይ ኃይል

      በአምላክ ቃል ውስጥ ደም ከሕይወት ጋር እኩል እንደሆነ ተደርጎ ተገልጿል። በመሆኑም በጥንቷ እስራኤል ይኖር የነበረ ንስሐ የገባ አንድ ኃጢአተኛ፣ የይሖዋን ትእዛዝ በመተላለፉ ፍርድ ከመቀበል ይልቅ በአምላክ መሠዊያ ላይ የእንስሳ መሥዋዕት ማቅረብ ይችል ነበር። (ዘሌዋውያን 4:27-31) ይህ መሥዋዕት የግለሰቡን ኃጢአት የሚያስተሰርይለት ቢሆንም የሚያገለግለው ለጊዜው ብቻ ነበር።

      በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ማስተሰረያ” የሚለው ቃል “ልዋጭ” የመሆንን እንዲሁም የአንድ ዕቃ ትክክለኛ ክዳን ዕቃውን ግጥም አድርጎ እንደሚከድነው ሁሉ “መሸፈኛ” የመሆንን ሐሳብ ያስተላልፋል። እርግጥ ነው፣ ማንኛውም እንስሳ የአንድን ሰው ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ‘ሊሸፍን’ ወይም ሊያስተሰርይ አይችልም። ይሁን እንጂ ጥንት ይቀርብ የነበረው የእንስሳት መሥዋዕት ወደፊት ለሚመጣው ፍጹም የሆነ የማስተሰረያ መሥዋዕት ጥላ ሆኖ አገልግሏል።​—ዕብራውያን 10:1, 4

      ይህ ማስተሰረያ የተገኘው “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖ በቀረበው የኢየሱስ ክርስቶስ አካል አማካኝነት” ነው። (ዕብራውያን 10:10) ‘ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም ባለ ውድ ደሙ’ የተወከለው የክርስቶስ ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወት፣ አዳም ካጣው ሕይወት ጋር ፍጹም ተመጣጣኝ ነበር። (1 ጴጥሮስ 1:19) በዚህ መንገድ በጣም በሚደነቅና ፍቅራዊ በሆነ መልኩ ፍትሕ ያለበት እርምጃ የተወሰደ ከመሆኑም በላይ እኛም “ዘላለማዊ መዳን” ማግኘት የምንችልበት መንገድ ተከፍቶልናል።​—ዕብራውያን 9:11, 12፤ ዮሐንስ 3:16፤ ራእይ 7:14

  • ልክ እንደ አምላክ ለሕይወት ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለህ?
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
    • a ሳይንቲፊክ አሜሪካን የተባለው መጽሔት፣ አምላክ “የፍጡር ሕይወት በደሙ ውስጥ ነው” ሲል የተናገረውን ሐሳብ በማስመልከት እንዲህ ብሏል:- “ምሳሌያዊ ትርጉሙን ብንተወው እንኳን ይህ አባባል ቃል በቃልም እውነት ነው:- ሁሉም ዓይነት የደም ሴል ለሕይወት የግድ አስፈላጊ ነው።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ