የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የአምላክ እስራኤል” እና “እጅግ ብዙ ሰዎች”
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ሐምሌ 1
    • 8 እስራኤላውያን ታማኝ በነበሩበት ወቅት የይሖዋን ሉዓላዊነት ከመገንዘባቸውም በተጨማሪ እንደ ንጉሣቸው አድርገው ተቀብለውት ነበር። (ኢሳይያስ 33:22) ስለዚህ አንድ መንግሥት ነበሩ። ይሁን እንጂ ቆየት ብሎ እንደተገለጸው ስለ “መንግሥት” የተሰጠው ተስፋ ከዚህ የበለጠም ትርጉም አለው። በተጨማሪም የይሖዋን ሕግ ሲታዘዙ ንጹሕ የሆኑና በዙሪያቸው ካሉት ሕዝቦች የተለዩ ነበሩ። ቅዱስ ሕዝብ ነበሩ። (ዘዳግም 7:5, 6) የካህናት መንግሥት ነበሩን? በእስራኤል ውስጥ የሌዊ ነገድ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ተመድቦ ነበር፤ በዚህ ነገድ ውስጥ ሌዋውያን የክህነት መብት ነበራቸው። የሙሴ ሕግ በሥራ ላይ መዋል ሲጀምር ሌዋውያን ወንዶች ሌዋዊ ባልሆነ የእያንዳንዱ ቤተሰብ በኩር ፈንታ ተወሰዱ።a (ዘጸአት 22:29፤ ዘኁልቁ 3:11–16, 40–51) በዚህ መንገድ በእስራኤል ያለ እያንዳንዱ ቤተሰብ በምሳሌያዊ ሁኔታ በቤተ መቅደስ ውስጥ በሚሰጠው አገልግሎት ተወክሎ ነበር። ይህ ውክልና ሕዝቡ ክህነት ያገኘበት መንገድ ነበር። ያም ሆነ ይህ ይሖዋን በብሔራት ፊት ወክለውታል። እውነተኛውን አምላክ ለማምለክ የሚፈልግ ማንኛውም የውጭ አገር ሰው ይህን ማድረግ የሚችለው ከእስራኤላውያን ጋር በመተባበር ነበር።—2 ዜና መዋዕል 6:32, 33፤ ኢሳይያስ 60:10

  • “የአምላክ እስራኤል” እና “እጅግ ብዙ ሰዎች”
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ሐምሌ 1
    • a የእስራኤል ክህነት በሥራ ላይ ሲውል ሌዋውያን ያልሆኑ የእስራኤል ነገዶች የበኩር ልጆችና የሌዊ ነገድ ወንዶች ተቆጠሩ። የእስራኤላውያን የበኩር ልጆች ቁጥር ከሌዊ ወንዶች ቁጥር በ273 በለጠ። ስለዚህ ለተረፉት ለ273ቱ ለእያንዳንዳቸው አምስት ሰቅል እንደ ቤዛ ሆኖ እንዲከፈል ይሖዋ አዘዘ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ