-
“ይሖዋ የእሱ የሆኑትን ያውቃል”መጠበቂያ ግንብ—2014 | ሐምሌ 15
-
-
4. ጳውሎስ ስለ ምን ነገር እርግጠኛ ነበር? ይህን ስሜቱን ለጢሞቴዎስ የገለጸለትስ እንዴት ነው?
4 ይሖዋ፣ ለእሱ በሚያቀርቡት አምልኮ ረገድ ግብዝ የሆኑ ሰዎችንም ሆነ ለእሱ ታዛዥ የሆኑትን ለይቶ እንደሚያውቅ ጳውሎስ እርግጠኛ ነበር። ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት ለጢሞቴዎስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ የተጠቀመባቸው ቃላት ስለዚህ ጉዳይ ምን ያህል እርግጠኛ እንደሆነ ያሳያሉ። ጳውሎስ፣ ከሃዲዎች በተወሰኑ የጉባኤው አባላት መንፈሳዊነት ላይ እያደረሱ ስላሉት ጉዳት ከገለጸ በኋላ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ይሁን እንጂ ‘ይሖዋ የእሱ የሆኑትን ያውቃል’ እንዲሁም ‘የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ’ የሚል ማኅተም ያለበት ጠንካራው የአምላክ መሠረት ጸንቶ ይኖራል።”—2 ጢሞ. 2:18, 19
-
-
“ይሖዋ የእሱ የሆኑትን ያውቃል”መጠበቂያ ግንብ—2014 | ሐምሌ 15
-
-
6 ጳውሎስ ስለ “ጠንካራው የአምላክ መሠረት” የገለጸው በዘኍልቍ 16:5 ላይ ሙሴ፣ ስለ ቆሬና ግብረ አበሮቹ ከተናገረው ሐሳብ ጋር አያይዞ ነው። ጳውሎስ በሙሴ ዘመን የተከናወነውን ሁኔታ የጠቀሰው ጢሞቴዎስን ሊያበረታታውና ይሖዋ የዓመፅ ድርጊትን እንደሚመለከት ብሎም እርምጃ እንደሚወስድ ሊያስታውሰው ፈልጎ እንደሆነ ግልጽ ነው። ከበርካታ ዘመናት በፊት ቆሬ የይሖዋን ዓላማ ማደናቀፍ እንዳልቻለ ሁሉ በጉባኤ ውስጥ የነበሩት ከሃዲዎችም ይህን ማድረግ አይችሉም። እርግጥ ጳውሎስ “ጠንካራው የአምላክ መሠረት” ምን እንደሚያመለክት በዝርዝር አልተናገረም። ይሁንና የተጠቀመባቸው ቃላት ጢሞቴዎስ፣ ይሖዋ ነገሮችን በሚያከናውንበት መንገድ ላይ እንዲተማመን እንደረዱት ጥርጥር የለውም።
-
-
“ይሖዋ የእሱ የሆኑትን ያውቃል”መጠበቂያ ግንብ—2014 | ሐምሌ 15
-
-
8, 9. ጳውሎስ በተጠቀመበት ምሳሌ ላይ ከገለጸው “ማኅተም” ምን ትምህርት እናገኛለን?
8 ጳውሎስ በ2 ጢሞቴዎስ 2:19 ላይ የተጠቀመበት ምሳሌያዊ አገላለጽ፣ መልእክት የተቀረጸበትን አንድ መሠረት እንድናስብ ያደርገናል፤ መልእክቱ መሠረቱ ላይ በማኅተም የታተመ ያህል ነው። በጥንት ጊዜ በአንድ ሕንፃ መሠረት ላይ ጽሑፍ መቅረጽ የተለመደ ነበር፤ ይህ የሚደረገው ሕንፃውን ማን እንደሠራው ወይም የማን ንብረት እንደሆነ ለመጠቆም ሊሆን ይችላል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች መካከል እንዲህ ያለ ምሳሌ የተጠቀመው የመጀመሪያው ሰው ጳውሎስ ነው።a ‘በጠንካራው የአምላክ መሠረት’ ላይ የተቀረጸው ማኅተም ሁለት መልእክቶችን የያዘ ነው። የመጀመሪያው “ይሖዋ የእሱ የሆኑትን ያውቃል” የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” ይላል። ይህም በዘኍልቍ 16:5 ላይ የሚገኘውን ጥቅስ ያስታውሰናል።—ጥቅሱን አንብብ።
-