የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • ከጥንቆላና ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች

      5. ከመናፍስታዊ ድርጊቶች ራቅ

      ሰይጣንና አጋንንቱ የይሖዋ ጠላቶች ናቸው። የእኛም ጠላቶች ናቸው። ሉቃስ 9:38-42⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • አጋንንት በሰዎች ላይ ምን ጉዳት ያደርሳሉ?

      አጋንንት በሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ መፍቀድ አይኖርብንም። ዘዳግም 18:10-12⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • አጋንንት በእኛ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ወይም ከእኛ ጋር ለመገናኘት የትኞቹን ዘዴዎች ይጠቀማሉ? አንተ በምትኖርበት አካባቢ የትኞቹን ልማዶች አስተውለሃል?

      • ይሖዋ መናፍስታዊ ድርጊቶችን መከልከሉ ምክንያታዊ እንደሆነ ይሰማሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

      ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ ‘ዲያብሎስን ተቃወሙት’ (5:02)

      • የፓሌሳ ልጅ ያደረገችው ክታብ ጉዳት ያለው ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

      • ፓሌሳ አጋንንት ከሚያሳድሩባት ተጽዕኖ ለመላቀቅ ምን ማድረግ ነበረባት?

      እውነተኛ ክርስቲያኖች ከጥንት ጊዜ አንስቶ አጋንንትን ሲቃወሙ ቆይተዋል። የሐዋርያት ሥራ 19:19⁠ን እና 1 ቆሮንቶስ 10:21⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ያለውን ማንኛውንም ነገር ማስወገድህ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

      አንዲት ሴት ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ግንኙነት ያላቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች ስታቃጥል
  • የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 2. ስለ ሞት እውነቱን ማወቃችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?

      ብዙ ሰዎች ሞትን አልፎ ተርፎም የሞቱ ሰዎችን ይፈራሉ! መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሞት የሚናገረውን ነገር ማወቅ ግን ያጽናናል። ኢየሱስ ‘እውነት ነፃ ያወጣችኋል’ ብሏል። (ዮሐንስ 8:32) አንዳንድ ሃይማኖቶች ሰው ከሞተ በኋላ በሕይወት መኖሯን የምትቀጥል የማትሞት ነፍስ እንዳለች ያስተምራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ አይልም። ማንም ሰው ከሞተ በኋላ አይሠቃይም። በተጨማሪም ሙታን ምንም ነገር ስለማያውቁ እኛን ሊጎዱን አይችሉም። እንዲሁም ከሞቱ ሰዎች ጋር በተያያዘ ለየት ያለ ሃይማኖታዊ ሥርዓት መፈጸም ወይም ስለ እነሱ መጸለይ አያስፈልገንም።

      አንዳንዶች ‘የሞቱ ሰዎችን ማነጋገር እንችላለን’ ይላሉ። ሆኖም ይህ ሊሆን የማይችል ነገር ነው። ቀደም ሲል እንደተመለከትነው ‘ሙታን ምንም አያውቁም።’ በሞት የተለዩአቸውን ሰዎች እንደሚያነጋግሩ የሚያስቡ ሰዎች የሚያነጋግሩት የሞቱትን ሰዎች ሳይሆን እነሱን መስለው የሚቀርቡ አጋንንትን ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሞትን በተመለከተ እውነቱን ማወቃችን ከአጋንንት ይጠብቀናል። ይሖዋ ከሞቱ ሰዎች ጋር ለመነጋገር መሞከር እንደሌለብን አስጠንቅቆናል፤ ምክንያቱም አጋንንት በዚህ ተጠቅመው ሊጎዱን እንደሚችሉ ያውቃል።—ዘዳግም 18:10-12⁠ን አንብብ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ