-
ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥቅምት 1
-
-
ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
-
-
ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥቅምት 1
-
-
ለይሖዋ በፈቃደኝነት መታዘዛችን በረከት ያስገኝልናል። ሙሴ ‘መልካም እንዲሆንልህ ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞች ጠብቅ’ በማለት ጽፏል። (ቁጥር 13) አዎን፣ ይሖዋ ማንኛውንም ትእዛዝ የሚሰጠን ማለትም ከእኛ የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር እንድንፈጽም የሚጠብቅብን ለእኛ መልካም እንዲሆንልን በማሰብ ነው። እንዲህ ብለን ማመናችን ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “አምላክ ፍቅር ነው” ይላል። (1 ዮሐንስ 4:8) ይሖዋ እነዚህን ትእዛዛት የሰጠው ዘላቂ ጥቅም እንድናገኝ በማሰብ ብቻ ነው። (ኢሳይያስ 48:17) ይሖዋ እንድናደርግ ያዘዘውን ነገር ሁሉ መፈጸማችን በአሁኑ ወቅት ተስፋ ከሚያስቆርጡ ብዙ ችግሮች የሚጠብቀን ሲሆን ወደፊት ደግሞ መንግሥቱ ምድርን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ማለቂያ የሌለው በረከት ያስገኝልናል።c
-