የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ልካቸውን በሚያውቁ ዘንድ ጥበብ ትገኛለች”
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ነሐሴ 1
    • 12. ጌዴዎን የተሰጠውን ተልእኮ በሚወጣበት ጊዜ ብልህነትን ያሳየው እንዴት ነው?

      12 ይሖዋ ጌዴዎንን ወደ ጦርነት ከመላኩ በፊት ፈተና አቀረበለት። እንዴት? ጌዴዎን አባቱ ያሠራውን የበኣል መሠዊያ እንዲያፈርስና ከመሠዊያው አጠገብ ተተክሎ የነበረውን የማምለኪያ ዐፀድ እንዲቆርጥ ተነገረው። ይህን ማድረግ ድፍረት የሚጠይቅ ነበር። ሆኖም ጌዴዎን የተሰጠውን ተልእኮ በሚያከናውንበት ጊዜ ልክን የማወቅንና የብልህነትን ባሕርይ አሳይቷል። ጌዴዎን ተልእኮውን በገሃድ ከመፈጸም ይልቅ የማንንም ትኩረት ሳይስብ ጨለማን ተገን በማድረግ የተባለውን አከናወነ። በተጨማሪም ጌዴዎን የተሰጠውን ተልእኮ በሚፈጽምበት ጊዜ ሁሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርጓል። መሠዊያውንና የማምለኪያ ዐፀዱን በሚያፈርስበት ጊዜ ግማሾቹ እንዲረዱት ሌሎቹ ደግሞ ፈንጠር ብለው አካባቢውን መቃኘት እንዲችሉ ሳይሆን አይቀርም ከእርሱ ጋር አሥር አገልጋዮችን ወሰደ።b ያም ሆነ ይህ ጌዴዎን በይሖዋ ድጋፍ የተሰጠውን ተልዕኮ ያከናወነ ሲሆን በኋላም አምላክ እስራኤልን ከምድያማውያን ነፃ እንዲያወጣ ተጠቅሞበታል።​—⁠መሳፍንት 6:​25-27

  • “ልካቸውን በሚያውቁ ዘንድ ጥበብ ትገኛለች”
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ነሐሴ 1
    • b ጌዴዎን ያሳየው ጥንቃቄና ብልህነት የፈሪነት ምልክት እንደሆነ ተደርጎ በስህተት ሊወሰድ አይገባውም። ከዚህ ይልቅ ደፋር መሆኑን በ⁠ዕብራውያን 11:​32-38 ላይ የተረጋገጠ ሲሆን እዚያም ላይ “ከድካማቸው በረቱ” እንዲሁም “በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ” ከተባለላቸው ሰዎች መካከል ጌዴዎንም አብሮ ተጠቅሷል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ