የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሐምሌ 1
    • ሁለቱ ሴቶች የቤተልሔምን ሕይወት ሲጀምሩ ሩት ራሷንም ሆነ ኑኃሚንን እንዴት እንደምታስተዳድር ሐሳብ ሆነባት። ይሖዋ በእስራኤል ለሚኖሩ ሕዝቦቹ በሰጠው ሕግ ውስጥ ድሆች የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንዲያገኙ የሚያስችል ፍቅራዊ ዝግጅት እንዳለ አወቀች። አዝመራ በሚሰበሰብበት ወቅት ድሆች ወደ ሌሎች ማሳ በመሄድ አጫጆቹን እየተከተሉ ከኋላ የወዳደቀውንና ከማሳው ዳርና ዳር የበቀለውን እንዲቃርሙ ይፈቀድላቸው ነበር።c​—ዘሌዋውያን 19:9, 10፤ ዘዳግም 24:19-21

      ጊዜው ገብስ የሚታጨድበት ወቅት ሲሆን በዘመናዊ የጊዜ አቆጣጠር መሠረት ወሩ ሚያዝያ ሳይሆን አይቀርም፤ ሩት በሕጉ ውስጥ በሰፈረው ዝግጅት መሠረት በማሳው ላይ እንድታቃርም የሚፈቅድላት ሰው ካለ በሚል ወደ እርሻው ቦታ ሄደች። እንዳጋጣሚ ሆኖ የሄደችበት እርሻ ባለቤት፣ የኑኃሚን ባል የሆነው የሟቹ የአቤሜሌክ ዘመድ የሆነ ቦዔዝ የተባለ ሀብታም ባለርስት ነበር። ምንም እንኳ ሩት በሕጉ መሠረት የመቃረም መብት ቢኖራትም ፈቃድ ሳትጠይቅ ሥራዋን አልጀመረችም፤ ከዚህ ይልቅ ወደ አጫጆቹ አለቃ ቀርባ መቃረም ትችል እንደሆነ ጠየቀችው። እሱም እንድትቃርም ሲፈቅድላት ወዲያውኑ ሥራዋን ጀመረች።​—ሩት 1:22 እስከ 2:3, 7

  • “ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሐምሌ 1
    • c ይህ፣ ሩት በትውልድ አገሯ ከምታውቀው ፈጽሞ የተለየ ግሩም ዝግጅት ነበር። በዚያ ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢዎች የሚኖሩ መበለቶች በደል ይደርስባቸው ነበር። አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “አንዲት ሴት ባሏ ከሞተ በኋላ በአብዛኛው ደጋፊና ጧሪ የሚሆኗት ወንዶች ልጆቿ ነበሩ፤ ወንዶች ልጆች ከሌሏት ግን ያላት አማራጭ ራሷን ለባርነት መሸጥ ወይም ዝሙት አዳሪ መሆን ነበር፤ አለዚያ ግን ትሞት ነበር።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ