የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 19, 20. (ሀ) ቦዔዝ ሩትን ወዲያውኑ ያላገባት ለምንድን ነው? (ለ) ቦዔዝ ለሩት ደግነት ያሳያት እንዲሁም ለስሜቷም ሆነ ለስሟ እንደሚጠነቀቅ ያሳየው እንዴት ነው?

      19 ቦዔዝ በመቀጠል እንዲህ አላት፦ “አሁንም ልጄ ሆይ፤ አትፍሪ፤ የምትጠይቂውን ሁሉ አደርግልሻለሁ፤ አንቺ ምግባረ መልካም ሴት መሆንሽንም የአገሬ ሰው ሁሉ ያውቀዋል።” (ሩት 3:11) ቦዔዝ፣ ሩትን የማግባት አጋጣሚ በማግኘቱ ደስ ብሎታል፤ ምናልባትም እሷን እንዲቤዣት ጥያቄ ሊቀርብለት እንደሚችል በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ጠብቆ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ቦዔዝ ጻድቅ ሰው ስለነበር ስለ ራሱ ፍላጎት ብቻ አላሰበም። በመሆኑም ከእሱ ይልቅ ለሟቹ የኑኃሚን ባል ቤተሰብ ይበልጥ ቅርብ የሆነ የመቤዠት ግዴታ ያለበት ሰው እንዳለ ለሩት ገለጸላት። ስለዚህ ቦዔዝ መጀመሪያ ይህን ሰው አግኝቶ እሷን ለማግባት ፈቃደኛ መሆን አለመሆኑን መጠየቅ ይኖርበታል።

      ሩት ለሌሎች ደግነትና አክብሮት በማሳየቷ መልካም ስም አትርፋለች

  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 21. ሩት መልካም ስም እንድታተርፍ አስተዋጽኦ ያደረገው ምንድን ነው? እኛስ የእሷን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

      21 ሩት፣ በሰው ሁሉ ዘንድ “ምግባረ መልካም ሴት” በመሆኗ እንደምትታወቅ ቦዔዝ የነገራትን መለስ ብላ ስታስብ ምን ያህል ተደስታ ይሆን! እንዲህ ያለ መልካም ስም እንድታተርፍ አስተዋጽኦ ያደረገው ይሖዋን ለማወቅና እሱን ለማገልገል ያላት ከፍተኛ ፍላጎት እንደሆነ ጥርጥር የለውም። በተጨማሪም ለእሷ ፈጽሞ እንግዳ የሆኑ ልማዶችንና ባሕሎችን ለመቀበል ፈቃደኛ በመሆን ለኑኃሚንም ሆነ ለሕዝቧ ታላቅ ደግነትና አሳቢነት አሳይታለች። እኛም ሩትን በእምነቷ የምንመስላት ከሆነ ለሰዎች አሳቢነት ለማሳየት እንዲሁም ባሕላቸውንና ልማዳቸውን በጥልቅ ለማክበር እንጥራለን። እንዲህ የምናደርግ ከሆነ እኛም ልክ እንደ ሩት መልካም ስም እናተርፋለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ