-
“ምግባረ መልካም ሴት”መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥቅምት 1
-
-
ቦዔዝ በመቀጠል እንዲህ አላት፦ “አሁንም ልጄ ሆይ፤ አትፍሪ፤ የምትጠይቂውን ሁሉ አደርግልሻለሁ፤ አንቺ ምግባረ መልካም ሴት መሆንሽንም የአገሬ ሰው ሁሉ ያውቀዋል” አላት። (ሩት 3:11) ቦዔዝ፣ ሩትን የማግባት አጋጣሚ በማግኘቱ ደስ ብሎታል፤ ምናልባትም እሷን እንዲቤዣት ጥያቄ እንደሚቀርብለት ጠብቆ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ቦዔዝ ጻድቅ ሰው በመሆኑ ስለ ራሱ ፍላጎት ብቻ አላሰበም። ከእሱ ይልቅ ከሟቹ የኑኃሚን ባል ጋር ይበልጥ የቀረበ ዝምድና ያለውና ሊቤዣት የሚችል ሌላ ሰው ስላለ መጀመሪያ ያንን ሰው ቀርቦ እሷን ለማግባት ፈቃደኛ መሆኑን እንደሚጠይቀው ለሩት ገለጸላት።
-
-
“ምግባረ መልካም ሴት”መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥቅምት 1
-
-
ሩት፣ በሰው ሁሉ ዘንድ “ምግባረ መልካም ሴት” በመሆኗ እንደምትታወቅ ቦዔዝ የነገራትን መለስ ብላ ስታስብ ምን ያህል ተደስታ ይሆን! ይሖዋን ለማወቅና እሱን ለማገልገል ያላት ጉጉት እንዲህ ያለ መልካም ስም እንድታተርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ጥርጥር የለውም። በተጨማሪም ለእሷ ፈጽሞ እንግዳ የሆኑ ልማዶችንና ባሕሎችን ለመቀበል ፈቃደኛ በመሆን ለኑኃሚንና ለሕዝቧ ታላቅ ደግነትና አሳቢነት አሳይታለች። እኛም ሩትን በእምነቷ የምንመስላት ከሆነ ለሌሎች እንዲሁም ለባሕላቸው ጥልቅ አክብሮት ለማሳየት እንጥራለን። እንዲህ ካደረግን እኛም እንደ ሩት በመልካም ምግባራችን ጥሩ ስም እናተርፋለን።
-