የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 3/1 ገጽ 23
  • ‘ይሖዋ ልብን ያያል’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ይሖዋ ልብን ያያል’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ዳዊትን መረጠው
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢኖሩም ጸንቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ለይሖዋ እንደ ልቡ የሆነለት ሰው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ሳሙኤል እውነተኛውን አምልኮ አስፋፍቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 3/1 ገጽ 23

ወደ አምላክ ቅረብ

‘ይሖዋ ልብን ያያል’

1 ሳሙኤል 16:1-12

ውጭያዊ መልክና ቁመና አሳሳች ሊሆን ይችላል። የአንድ ሰው ውጭያዊ ገጽታ ውስጣዊ ማንነቱን ማለትም ልቡን በትክክል ላይገልጽ ይችላል። ሰዎች ውጭያዊ መልክና ቁመና አይተው መፍረድ ይቀናቸዋል። ደስ የሚለው ግን ይሖዋ አምላክ ከአንድ ሰው ውጭያዊ መልክ ባሻገር ያለውን ይመለከታል። በ1 ሳሙኤል 16:1-12 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ሐሳብ ይህን ሐቅ በግልጽ አስቀምጦልናል።

እስቲ የሚከተለውን ሁኔታ በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት። ይሖዋ በእስራኤል ብሔር ላይ አዲስ ንጉሥ ሊሾም ነው። አምላክ ነቢዩ ሳሙኤልን ‘ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ እልክሃለሁ፤ ምክንያቱም ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ’ አለው። (ቁጥር 1) ይሖዋ ከእሴይ ልጆች መካከል አንዱን ንጉሥ አድርጎ እንደሚመርጥ ተናገረ እንጂ ስም አልጠቀሰም። ሳሙኤል ወደ ቤተልሔም እየሄደ ሳለ ‘ከእሴይ ልጆች መካከል ይሖዋ የመረጠው ማንን እንደሆነ እንዴት አውቃለሁ?’ ብሎ አስቦ ሊሆን ይችላል።

ሳሙኤል ቤተልሔም ከደረሰ በኋላ መሥዋዕት አዘጋጅቶ እሴይንና ልጆቹን ጠራቸው። የእሴይ የመጀመሪያ ልጅ የሆነው ኤልያብ ሲገባ ሳሙኤል በቁመናው በጣም ተማረከ። ሳሙኤል፣ ኤልያብ የንጉሥነት ግርማ እንዳለው ስለተሰማው “በእርግጥ እግዚአብሔር የቀባው ሰው እነሆ፤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞአል” ብሎ ከራሱ ጋር አወራ።—ቁጥር 6

ይሖዋ ግን ነገሮችን የሚመለከተው በተለየ መንገድ ነው። ሳሙኤልን “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁ” አለው። (ቁጥር 7) ይሖዋ በኤልያብ ቁመትና ውበት አልተማረከም። ሁሉን ነገር ማየት የሚችለው የይሖዋ ዓይን፣ ያረፈው ከውጭያዊ ቁመና ባሻገር ባለው እውነተኛ ውበት ላይ ነው።

ይሖዋ ለሳሙኤል “እግዚአብሔር የሚያየው፣ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው። (ቁጥር 7) አዎን፣ ይሖዋ ትልቅ ግምት የሚሰጠው የአንድ ሰው ሐሳብ፣ ዝንባሌና ስሜት ምንጭ ለሆነው ውስጣዊ ማንነት ይኸውም ለልብ ነው። ‘ልብን የሚመረምረው’ ይሖዋ ኤልያብንም ሆነ ከእሱ በኋላ ሳሙኤል ፊት የቀረቡትን ስድስቱን የእሴይ ልጆች አልመረጣቸውም።—ምሳሌ 17:3

እሴይ ዳዊት የሚባል የመጨረሻ ልጅ ነበረው፤ በዚያ ጊዜ ዳዊት “በጎች እየጠበቀ” ነበር። (ቁጥር 11) በመሆኑም ዳዊት ተጠርቶ ከመጣ በኋላ ሳሙኤል ፊት ቀረበ። ከዚያም ይሖዋ ለሳሙኤል “የመረጥሁት ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው” አለው። (ቁጥር 12) እርግጥ ዳዊት “ደም ግባት ያለው፣ ዐይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበረ።” ይሁንና በአምላክ ፊት ሞገስ እንዲያገኝ ያስቻለው ልቡ ነበር።—1 ሳሙኤል 13:14

ለውጭያዊ ውበት ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጠው በዚህ ዓለም ውስጥ ይሖዋ አምላክ በውጭያዊ ውበት እንደማይታለል ማወቃችን ያጽናናናል። ረጅም ሆንክም አልሆንክ አሊያም ሰዎች መልከ መልካም ወይም ቆንጆ አድርገው ተመለከቱህም አልተመለከቱህም በይሖዋ ዘንድ የሚያመጣው ለውጥ የለም። ይሖዋ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ለውስጣዊ ማንነትህ ወይም ለልብህ ነው። ታዲያ ይህን ማወቅህ በይሖዋ ዓይን ውብ ሆነህ እንድትታይ የሚያደርጉህን ባሕርያት እንድታዳብር አይገፋፋህም?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ