-
“ውጊያው የይሖዋ ነው”መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 5
-
-
ዳዊት ጎልያድን አስመልክቶ “በዚህ ሰው የተነሳ የማንም ሰው ልብ አይቅለጥ” በማለት ለሳኦል አበረታች ሐሳብ ተናገረ። ደግሞም ሳኦልና አብረውት ያሉት ሰዎች በጎልያድ የተነሳ ወኔ ከድቷቸው ነበር። እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ከዚያ ግዙፍ ሰው ጋር አወዳድረው ይሆናል፤ ምናልባትም ቁመታቸው ሆዱ ወይም ደረቱ ጋር እንኳ እንደማይደርስ ተሰምቷቸው በፍርሃት ሳይርዱ አልቀረም። የጦር ልብስ የለበሰው ይህ ግዙፍ ሰው በቀላሉ እንደሚጨፈልቃቸው ተሰምቷቸዋል። ዳዊት ግን እንደዚህ አላሰበም። በኋላ ላይ እንደምንመለከተው እሱ ሁኔታውን ያየው ፈጽሞ በተለየ መንገድ ነው። በመሆኑም ጎልያድን መግጠም እንደሚፈልግ ተናገረ።—1 ሳሙኤል 17:32
-
-
“ውጊያው የይሖዋ ነው”መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 5
-
-
ዳዊት የጎልያድን ግዝፈት ወይም የጦር መሣሪያዎች ሳያይ ቀርቶ አይደለም። ሆኖም ዳዊት እነዚህ ነገሮች ወኔውን እንዲሰልቡበት አልፈቀደም። ሳኦልና ሠራዊቱ የፈጸሙትን ስህተት አልደገመም። ራሱን ከጎልያድ ጋር አላነጻጸረም። ከዚህ ይልቅ ጎልያድን የተመለከተው ከይሖዋ አንጻር ነው። ጎልያድ ቁመቱ 2.9 ሜትር በመሆኑ ከሰዎች ጋር ሲወዳደር ተራራ ሊመስል ይችላል፤ ያም ቢሆን ከአጽናፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዢ ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በእርግጥም ጎልያድ ከይሖዋ ጋር ሲወዳደር እንደማንኛውም ሰው ከአንዲት ትንኝ አይበልጥም፤ በመሆኑም ይሖዋ በቀላሉ ሊጨፈልቀው ይችላል!
ዳዊት ከኮረጆው ውስጥ ድንጋይ እያወጣ ወደ ጠላቱ ሮጠ። ድንጋዩን ወንጭፉ ላይ በማስቀመጥ እጁን ከፍ አድርጎ ወንጭፉን በኃይል ማሽከርከር ጀመረ። ጎልያድም ምናልባትም ከጋሻ ጃግሬው ኋላ ሆኖ ወደ ዳዊት ገሰገሰ። ጎልያድ ቁመቱ ረጅም መሆኑ ሳይጎዳው አልቀረም፤ ምክንያቱም ጋሻ ጃግሬው ቁመቱ እንደማንኛውም ሰው ስለሆነ በያዘው ጋሻ የጎልያድን ራስ መከለል አልቻለም። ዳዊት ያነጣጠረውም በጎልያድ ራስ ላይ ነበር።—1 ሳሙኤል 17:41
ዳዊት የትኛውም ግዙፍ ሰው ቢሆን ከይሖዋ ጋር ሲወዳደር ኢምንት እንደሆነ ተገንዝቧል
-
-
ዳዊትና ጎልያድ—ታሪኩ እውነት ነው?መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 5
-
-
1 | በእርግጥ 2.9 ሜትር ገደማ ርዝመት ያለው ሰው ሊኖር ይችላል?
መጽሐፍ ቅዱስ የጎልያድ ቁመት “ስድስት ክንድ ከአንድ ስንዝር” እንደነበረ ይናገራል። (1 ሳሙኤል 17:4) እዚህ ላይ የተጠቀሰው ክንድ 44.5 ሳንቲ ሜትር ርዝመት አለው፤ ስንዝር ደግሞ 22.2 ሳንቲ ሜትር ርዝመት አለው። ስለዚህ ጥቅሱ ላይ የተገለጹትን አኃዞች ስንደምራቸው 2.9 ሜትር ይሆናሉ። አንዳንዶች ጎልያድ ያን ያህል ርዝመት ሊኖረው እንደማይችል ይናገራሉ፤ ይሁን እንጂ እስቲ አንድ ምሳሌ እንመልከት፦ በዘመናችን የዓለማችን ረጅም ሰው ተብሎ በታሪክ መዝገብ የሠፈረው ሰው ቁመቱ 2.7 ሜትር ነው። ታዲያ ከዚህ ሰው በ15 ሳንቲ ሜትር ብቻ የሚበልጠው የጎልያድ ቁመት ለማመን የሚከብድ ነው? ጎልያድ የረፋይም ጎሳ ተወላጅ ሲሆን እነዚህ ሰዎች በጣም ግዙፍ በመሆናቸው ይታወቃሉ። በ13ኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. የተዘጋጀ አንድ የግብፃውያን ሰነድ፣ በከነዓን ክልል የነበሩ አንዳንድ አስፈሪ ጦረኞች ቁመታቸው ከ2.4 ሜትር በላይ እንደነበረ ይጠቅሳል። እርግጥ የጎልያድ ቁመት ያልተለመደ ነው፤ ሆኖም ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ግን አይደለም።
-