-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
9, 10. (ሀ) ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሕይወታቸውን ለማቆየት ምን ትግል ማድረግ ነበረባቸው? (ለ) ናባል ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ላደረጉለት ነገር አመስጋኝ መሆን ይገባው ነበር የምንለው ለምንድን ነው? (አንቀጽ 10 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻም ተመልከት።)
9 ናባል የሚኖረው በማዖን ሲሆን የሚሠራው ግን በአቅራቢያው በሚገኘው በቀርሜሎስ ነበር፤a እንዲያውም በዚህ አካባቢ መሬት የነበረው ይመስላል። እነዚህ ከተሞች ለበግ እርባታ አመቺ የሆኑ በከፍታ ቦታ ላይ የሚገኙ የግጦሽ መሬቶች የነበሯቸው ሲሆን ናባል ደግሞ 3,000 በጎች ነበሩት። በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበረው አካባቢ ግን ያልለማ ነበር። በስተ ደቡብ ሰፊ የሆነው የፋራን ምድረ በዳ ይገኛል። በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘው እስከ ጨው ባሕር ድረስ ያለው አካባቢ ደግሞ ገደላ ገደልና ዋሻ የበዛበት ጠፍ መሬት ነበር። ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች በዚህ አስቸጋሪ አካባቢ ሕይወታቸውን ለማቆየት ትግል ማድረግ ነበረባቸው፤ ምናልባትም የሚበሉትን ለማግኘት ማደን ብሎም ሌሎች በርካታ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን መቋቋም አስፈልጓቸው ይሆናል። እነዚህ ሰዎች ባለጸጋ የሆነውን የናባልን በጎች ከሚጠብቁት እረኞች ጋር በተደጋጋሚ የመገናኘት አጋጣሚ ነበራቸው።
-