የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለች
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 12 ናባል የዳዊትን መልእክት ሲሰማ በጣም ተቆጣ! በመግቢያው ላይ የጠቀስነው ወጣት በወቅቱ የተፈጠረውን ሁኔታ ለአቢግያ ሲነግራት፣ ናባል በመልእክተኞቹ ላይ ‘የስድብ ናዳ እንዳወረደባቸው’ ገልጾ ነበር። ስስታም የሆነው ናባል እንጀራውን፣ ውኃውንና ያረደውን ፍሪዳ ለማንም እንደማይሰጥ በቁጣ ገለጸ። ዳዊትን እንደማይረባ ሰው በመቁጠር ያፌዘበት ከመሆኑም ሌላ ከጌታው እንደኮበለለ አገልጋይ አድርጎ ተመልክቶታል። ናባል የነበረው አመለካከት ዳዊትን ይጠላው ከነበረው ከሳኦል የተለየ አልነበረም ማለት ይቻላል። ሁለቱም ቢሆኑ ይሖዋ ለዳዊት ያለው ዓይነት አመለካከት አልነበራቸውም። አምላክ፣ ዳዊትን ይወደው የነበረ ከመሆኑም ሌላ እንደ አንድ ዓመፀኛ ባሪያ ሳይሆን የእስራኤል የወደፊት ንጉሥ እንደሆነ አድርጎ ይመለከተው ነበር።—1 ሳሙ. 25:10, 11, 14

  • አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለች
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 14. (ሀ) አቢግያ ናባል የፈጠረውን ችግር ለማስተካከል የመጀመሪያውን እርምጃ ወስዳለች ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? (ለ) ናባልና አቢግያ ከነበራቸው የባሕርይ ልዩነት ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።)

      14 ቀደም ሲል እንደተመለከትነው አቢግያ የተፈጠረውን ከባድ ችግር ለማስተካከል የመጀመሪያውን እርምጃ ወስዳለች ማለት ይቻላል። ከባሏ ከናባል በተለየ መልኩ አቢግያ፣ ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነበረች። ወጣቱ አገልጋይ ስለ ናባል ሲናገር “እርሱ እንደ ሆነ . . . ባለጌ [“ምናምንቴ፣” የ1954 ትርጉም] ሰው ስለሆነ፣ ደፍሮ የሚነግረው አንድም ሰው የለም” ብሎ ነበር።c (1 ሳሙ. 25:17) የሚያሳዝነው፣ ናባል ራሱን ከፍ አድርጎ ስለሚመለከት ሌሎች የሚሉትን አይሰማም ነበር። በዛሬው ጊዜም ብዙዎች እንዲህ ዓይነት የእብሪተኝነት ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ወጣቱ አገልጋይ፣ አቢግያ ከዚህ የተለየ አመለካከት ያላት ሴት እንደሆነች ያውቅ ነበር፤ የተፈጠረውን ችግር ለእሷ የነገራትም ለዚህ ሳይሆን አይቀርም።

      ከናባል በተለየ መልኩ አቢግያ ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነበረች

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ