-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችመጠበቂያ ግንብ—2009 | ሐምሌ 1
-
-
በእምነታቸው ምሰሏቸው
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለች
አቢግያን ባነጋገራት ወጣት ፊት ላይ ፍርሃት ይነበባል። ወጣቱ ብርክ ይዞታል፤ ካንዣበበው ከባድ አደጋ አንጻር የዚህን ያህል መረበሹ ምንም አያስገርምም። ይህ ወጣት አቢግያን እያነጋገራት ሳለ 400 የሚሆኑ ጦረኞች በአቢግያ ባል በናባል ቤተሰብ ውስጥ የሚገኙ ወንዶችን አንድም ሳያስቀሩ ለማጥፋት ቆርጠው በመነሳት ወደ ናባል ቤት እየገሰገሱ ነበር። ለምን?
ችግሩን የቆሰቆሰው ናባል ነበር። ወደ እሱ የመጡትን ሰዎች ያነጋገራቸው ጸያፍ በሆነና በሚያዋርድ መንገድ ነበር፤ ናባል እንዲህ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዚህ ወቅት ግን ትልቅ ስህተት ሠርቷል፤ ናባል የተሳደበው በሚገባ የሠለጠኑና ታማኝ የሆኑ ተዋጊዎች ያሉትን ተወዳጅ መሪ ነው። ከናባል ሠራተኞች፣ ምናልባትም ከእረኞቹ አንዱ ወደ አቢግያ የመጣው በዚህ ወቅት ነበር። ወጣቱ፣ አቢግያ እነሱን ለማዳን አንድ መላ እንደምትፈጥር ተስፋ አድርጎ ነበር። ይሁንና አንዲት ሴት እነዚህን ጦረኞች ለማስቆም ምን ማድረግ ትችላለች?
-
-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችመጠበቂያ ግንብ—2009 | ሐምሌ 1
-
-
“የስድብ ናዳ አወረደባቸው”
ናባል በዚህ ወቅት የወሰደው እርምጃ የአቢግያ ሕይወት ይበልጥ አስቸጋሪ እንዲሆን የሚያደርግ ነበር። የሰደበው ታዋቂ ሰው የሆነውን ዳዊትን ነው። ዳዊት፣ ሳኦልን ተክቶ ንጉሥ እንዲሆን አምላክ የመረጠውና ነቢዩ ሳሙኤል የቀባው ታማኝ የይሖዋ አገልጋይ ነበር። (1 ሳሙኤል 16:1, 2, 11-13) ንጉሥ ሳኦል በቅንዓት ተነሳስቶ ዳዊትን ሊገድለው ያሳድደው ስለነበር ዳዊት ከንጉሡ ሸሽቶ ከ600 ታማኝ ተዋጊዎቹ ጋር በምድረ በዳ እየኖረ ነበር።
-
-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችመጠበቂያ ግንብ—2009 | ሐምሌ 1
-
-
ናባል የዳዊትን መልእክት ሲሰማ በቁጣ ደነፋ! በመግቢያው ላይ የጠቀስነው ወጣት በወቅቱ የተፈጠረውን ሁኔታ ለአቢግያ ሲነገራት፣ ናባል በመልእክተኞቹ ላይ ‘የስድብ ናዳ እንዳወረደባቸው’ ገልጾ ነበር። ገብጋባ የሆነው ናባል እንጀራውን፣ ውኃውንና ያረደውን ፍሪዳ መስጠት እንደማይፈልግ በቁጣ ገለጸ። ዳዊትን እንደማይረባ ሰው አድርጎ ያቃለለው ከመሆኑም ሌላ ከጌቶቻቸው ከኮበለሉ አገልጋዮች እንደ አንዱ ቆጥሮታል። ናባል የነበረው አመለካከት ዳዊትን ይጠላው ከነበረው ከሳኦል የተለየ አልነበረም ለማለት ይቻላል። ሁለቱም ቢሆኑ ይሖዋ ለዳዊት ያለው ዓይነት አመለካከት አልነበራቸውም። አምላክ፣ ዳዊትን የሚወደው ከመሆኑም በላይ እንደ አንድ ዓመፀኛ ባሪያ ሳይሆን የእስራኤል የወደፊት ንጉሥ እንደሆነ አድርጎ ይመለከተው ነበር።—1 ሳሙኤል 25:10, 11, 14
-
-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችመጠበቂያ ግንብ—2009 | ሐምሌ 1
-
-
ቀደም ሲል እንደተመለከትነው አቢግያ የተፈጠረውን ከባድ ችግር ለማስተካከል የመጀመሪያውን እርምጃ ወስዳለች ማለት ይቻላል። ከባሏ ከናባል በተለየ መልኩ አቢግያ፣ ወጣቱ የሚነግራትን ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነበረች። ወጣቱ አገልጋይ ስለ ናባል ሲናገር “እርሱ እንደ ሆነ . . . ባለጌ [“ምናምንቴ፣” የ1954 ትርጉም] ሰው ስለሆነ፣ ደፍሮ የሚነግረው አንድም ሰው የለም” ብሎ ነበር።c (1 ሳሙኤል 25:17) የሚያሳዝነው፣ ናባል ራሱን ከፍ አድርጎ ስለሚመለከት ሌሎች የሚሉትን አይሰማም ነበር። በዛሬው ጊዜም ብዙዎች እንዲህ ዓይነት የእብሪተኝነት ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ወጣቱ አገልጋይ፣ አቢግያ ከዚህ የተለየ አመለካከት ያላት ሴት እንደሆነች ያውቅ ነበር፤ የተፈጠረውን ችግር ለእሷ የነገራትም ለዚህ ሳይሆን አይቀርም።
-