-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
10 ታታሪ የነበሩት የዳዊት ወታደሮች ከእረኞቹ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ምን ይመስላል? የዳዊት ወታደሮች በፈለጉት ጊዜ ከናባል መንጋ በጎችን መዝረፍ ይችሉ ነበር፤ እነሱ ግን እንዲህ አላደረጉም። እንዲያውም እንደ አጥር በመሆን የናባልን መንጎችና እረኞች ከጥቃት ጠብቀዋቸዋል። (1 ሳሙኤል 25:15, 16ን አንብብ።) በጎችም ሆኑ እረኞች ለአደጋ የተጋለጡ ነበሩ። በአካባቢው አውሬዎች በብዛት ይገኙ የነበረ ከመሆኑም ሌላ ቦታው ለእስራኤል ደቡባዊ ድንበር ቅርብ በመሆኑ ከባዕድ አገር የሚመጡ ወንበዴዎችና ዘራፊዎች ብዙ ጊዜ ጥቃት ይሰነዝሩ ነበር።b
-
-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
b ዳዊት በአካባቢው የነበሩትን ባለርስቶችና መንጎቻቸውን ከጥቃት መጠበቅን ይሖዋ አምላክን እንደማገልገል አድርጎ ሳይቆጥረው አልቀረም። በዚያ ዘመን የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ ዝርያዎች በዚያ አካባቢ እንዲኖሩ የይሖዋ ዓላማ ነበር። በመሆኑም ይህን አካባቢ ከባዕድ አገር ወራሪዎችና ዘራፊዎች ጥቃት መጠበቅ ለይሖዋ የሚቀርብ ቅዱስ አገልግሎት እንደሆነ ተደርጎ ይታይ ነበር።
-