-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
14. (ሀ) አቢግያ ናባል የፈጠረውን ችግር ለማስተካከል የመጀመሪያውን እርምጃ ወስዳለች ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? (ለ) ናባልና አቢግያ ከነበራቸው የባሕርይ ልዩነት ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።)
14 ቀደም ሲል እንደተመለከትነው አቢግያ የተፈጠረውን ከባድ ችግር ለማስተካከል የመጀመሪያውን እርምጃ ወስዳለች ማለት ይቻላል። ከባሏ ከናባል በተለየ መልኩ አቢግያ፣ ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነበረች። ወጣቱ አገልጋይ ስለ ናባል ሲናገር “እርሱ እንደ ሆነ . . . ባለጌ [“ምናምንቴ፣” የ1954 ትርጉም] ሰው ስለሆነ፣ ደፍሮ የሚነግረው አንድም ሰው የለም” ብሎ ነበር።c (1 ሳሙ. 25:17) የሚያሳዝነው፣ ናባል ራሱን ከፍ አድርጎ ስለሚመለከት ሌሎች የሚሉትን አይሰማም ነበር። በዛሬው ጊዜም ብዙዎች እንዲህ ዓይነት የእብሪተኝነት ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ወጣቱ አገልጋይ፣ አቢግያ ከዚህ የተለየ አመለካከት ያላት ሴት እንደሆነች ያውቅ ነበር፤ የተፈጠረውን ችግር ለእሷ የነገራትም ለዚህ ሳይሆን አይቀርም።
ከናባል በተለየ መልኩ አቢግያ ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነበረች
-
-
አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለችበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
c ወጣቱ አገልጋይ ናባልን ለመግለጽ የተጠቀመበት ሐረግ ቃል በቃል ሲተረጎም “የቤልሆር (የከንቱነት) ልጅ” የሚል ፍቺ አለው። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን ዓረፍተ ነገር ሲተረጉሙ ናባል “ማንንም የማይሰማ” ሰው መሆኑን የሚያሳይ መግለጫ የሚጨምሩ ሲሆን ይህም “ለእሱ መናገር ምንም ዋጋ የለውም” ወደሚል መደምደሚያ ያደርሳል።
-