የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለች
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ሐምሌ 1
    • ቀደም ሲል እንደተመለከትነው አቢግያ የተፈጠረውን ከባድ ችግር ለማስተካከል የመጀመሪያውን እርምጃ ወስዳለች ማለት ይቻላል። ከባሏ ከናባል በተለየ መልኩ አቢግያ፣ ወጣቱ የሚነግራትን ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነበረች። ወጣቱ አገልጋይ ስለ ናባል ሲናገር “እርሱ እንደ ሆነ . . . ባለጌ [“ምናምንቴ፣” የ1954 ትርጉም] ሰው ስለሆነ፣ ደፍሮ የሚነግረው አንድም ሰው የለም” ብሎ ነበር።c (1 ሳሙኤል 25:17) የሚያሳዝነው፣ ናባል ራሱን ከፍ አድርጎ ስለሚመለከት ሌሎች የሚሉትን አይሰማም ነበር። በዛሬው ጊዜም ብዙዎች እንዲህ ዓይነት የእብሪተኝነት ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ወጣቱ አገልጋይ፣ አቢግያ ከዚህ የተለየ አመለካከት ያላት ሴት እንደሆነች ያውቅ ነበር፤ የተፈጠረውን ችግር ለእሷ የነገራትም ለዚህ ሳይሆን አይቀርም።

  • አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለች
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ሐምሌ 1
    • c ወጣቱ አገልጋይ ናባልን ለመግለጽ የተጠቀመበት ሐረግ ቃል በቃል ሲተረጎም “የክፋት (የከንቱነት) ልጅ” የሚል ፍቺ አለው። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን ዓረፍተ ነገር ሲተረጉሙ ናባልን “የማንንም ምክር የማይሰማ” ሰው እንደሆነ አድርገው የገለጹት ከመሆኑም ሌላ “ለእሱ መናገር ምንም ዋጋ የለውም” የሚል መግለጫ ይዘዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ