የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 5/1 ገጽ 32
  • ክፉን ማሸነፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ክፉን ማሸነፍ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 5/1 ገጽ 32

ክፉን ማሸነፍ

“ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ስለ ምን ይረግማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው።” ይህን ሐሳብ ያቀረበው የእስራኤል የጦር መሪ የነበረው አቢሳ ነበር። አቢሳ ይህን ቁጣ የተሞላበት ምላሽ የሰጠው ሳሚ የተባለው ብንያማዊ ጌታውን ንጉሥ ዳዊትን በጥላቻ ስሜት በሰደበው ጊዜ ነበር።​—⁠2 ሳሙኤል 16:​5-9

አቢሳ በዛሬው ጊዜ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለውን ፍልስፍና ማለትም ክፉን በክፉ የሚለውን ፈሊጥ ተግባራዊ ማድረግ ፈልጎ ነበር። አዎን፣ ሳሚ በዳዊት ላይ ላወረደው የስድብ ናዳ አቢሳ ሊበቀለው ፈልጎ ነበር።

ሆኖም ዳዊት ምን ምላሽ ሰጠ? ዳዊት “ተዉት” በማለት አቢሳን እርምጃ እንዳይወስድ ከለከለው። ምንም እንኳ ዳዊት ሳሚ ከሰነዘረበት ክስ ነጻ ቢሆንም ትሕትና በማሳየት የአጸፋ እርምጃ ከመውሰድ ታቅቧል። ከዚህ ይልቅ ጉዳዩን በይሖዋ እጅ ጥሏል።​—⁠2 ሳሙኤል 16:​10-13

ዳዊት ልጁ የሞከረበት ግልበጣ በመክሸፉ ሸሽቶ ከሄደበት ወደ ዙፋኑ ሲመለስ እርሱን ለመቀበልና ምሕረት ለመጠየቅ በቅድሚያ ከመጡት ሰዎች መካከል ሳሚ ይገኝበታል። በዚህ ጊዜም አቢሳ ሊገድለው ፈልጎ ነበር፤ ሆኖም ዳዊት በድጋሚ ከለከለው።​—⁠2 ሳሙኤል 19:​15-23

በዚህ ሁኔታ ዳዊት ተስማሚ በሆነ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስን ይወክላል። ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም . . . ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ።”​—⁠1 ጴጥሮስ 2:​23

በዛሬው ጊዜ ክርስቲያኖች ‘ትሑታን እንዲሆኑና ክፉን በክፉ ፈንታ እንዳይመልሱ’ ተመክረዋል። (1 ጴጥሮስ 3:​8, 9) ዳዊትና ኢየሱስ ክርስቶስ የተዉልንን ምሳሌ በመከተል እኛም ‘ክፉውን በመልካም ማሸነፍ’ እንችላለን።​—⁠ሮሜ 12:​17-21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ