የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረችው ኢየሩሳሌም—የአርኪኦሎጂ ውጤቶች ምን ይላሉ?
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ሰኔ 15
    • እዚሁ ግንብ አጠገብ የከተማዋ ጥንታዊ የውኃ መውረጃ በሮች ይገኛሉ፤ የዚህ የውኃ መውረጃ የተወሰነው ክፍል ከዳዊት ዘመን ጀምሮ የነበረ ይመስላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ስለ ኢየሩሳሌም የውኃ መውረጃ የሚናገሩት አንዳንድ ሐሳቦች ጥያቄ አስነስተዋል። ለምሳሌ ያህል ዳዊት አብረውት ለነበሩት “ኢያቡሳውያንንም የሚመታ በውኃ መሄጃው ይውጣ” ጠላትንም ‘ያውጣ’ ሲል ተናግሯል። (2 ሳሙኤል 5:​8) ይህንን ያደረገው የዳዊት የጦር አዛዥ የነበረው ኢዮአብ ነው። ‘የውኃ መሄጃ’ ሲል ምንን ለመግለጽ ነው?

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረችው ኢየሩሳሌም—የአርኪኦሎጂ ውጤቶች ምን ይላሉ?
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ሰኔ 15
    • ምሁራን የጥንቷ ከተማ በአብዛኛው ውኃ ታገኝ የነበረው ከግዮን ምንጭ እንደነበር ከተገነዘቡ ቆይተዋል። ከከተማዋ ቅጥር ውጭ ይገኝ የነበረ ቢሆ​ንም ብዙም ሩቅ ስላልነበር አንድ የውኃ መውረጃና 11 ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ በቁፋሮ ሊገኝ ችሏል፤ ይህም ነዋሪዎቹ ከከተማዋ መከላከያ ቅጥር ሳይወጡ ውኃ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል። ይህ የውኃ መስመር በ1867 ለመጀመሪያ ጊዜ ባገኙት በቻርለስ ዋረን ስም የዋረን ጉድጓድ ተብሎ ተሰይሟል። ይሁን እንጂ ይህ የውኃ መውረጃና ጉድጓዱ የተሠሩት መቼ ነበር? በዳዊት ዘመን ነበሩን? ኢዮአብ የተጠቀመበት የውኃ መውረጃ ይህ ነበርን? ዳን ጊል እንዲህ ሲሉ መልስ ይሰጣሉ:- “የዋረን ጉድጓድ ተፈጥሮአዊ ሽንቁር መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ወጣ ገባ ከሆነው ግድግዳ ላይ የካልካሪየስ ቅርፊት ወስደን በካርቦን 14 መርምረነው ነበር። ምንም አልነበረውም፤ ይህ ደግሞ ቅርፊቱ ከ40,000 የሚበልጡ ዓመታት እንደቆየ የሚያሳይ በመሆኑ ጉድጓዱ በሰው የተቆፈረ ነው ለማለት ፈጽሞ እንደማይቻል የማያሻማ ማረጋገጫ ይሰጣል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ