-
በንቃትና በትዕግሥት ተጠባብቋልመጠበቂያ ግንብ—2008 | ሚያዝያ 1
-
-
ኤልያስ ወደ አክዓብ ሄዶ፣ “የከባድ ዝናብ ድምፅ ይሰማልና ሂድና ብላ፤ ጠጣም” አለው። (ቁጥር 41) ይህ ክፉ ንጉሥ በዕለቱ ከተከናወኑት ነገሮች ያገኘው ትምህርት ይኖር ይሆን? ዘገባው ስለዚህ ጉዳይ በቀጥታ አይናገርም፤ ሆኖም አክዓብ ንስሐ እንደገባ የሚያሳይ አንድም ቃል የለም፤ እንዲሁም ወደ ይሖዋ ለመቅረብና ምሕረት ለማግኘት የነቢዩን እርዳታ እንደጠየቀ የሚናገር ምንም ሐሳብ አናገኝም። ዘገባው፣ አክዓብ “ሊበላና ሊጠጣ ሄደ” ስለሚል ከዚህ ውጭ ያደረገው ነገር የለም። (ቁጥር 42) ኤልያስስ ምን አድርጎ ይሆን?
-
-
በንቃትና በትዕግሥት ተጠባብቋልመጠበቂያ ግንብ—2008 | ሚያዝያ 1
-
-
ኤልያስ፣ ይሖዋ እርምጃ የሚወስድበት ጊዜ መድረሱን የሚያሳይ አንድ የሆነ ፍንጭ ለማየት ጓጉቶ ነበር። በመሆኑም አገልጋዩን ምቹ ወደሆነ አንድ ከፍታ ላይ በመውጣት እንደሚዘንብ የሚጠቁም ምልክት መኖር አለመኖሩን እንዲያይ ላከው። አገልጋዩ፣ “በዚያ ምንም የለም” የሚል ተስፋ አስቆራጭ ሪፖርት ይዞ ተመለሰ። አድማሱ የጠራ ከመሆኑም በላይ በግልጽ እንደሚታየው በሰማይም ላይ ምንም ደመና አልነበረም። ጥያቄ የሚፈጥር አንድ ነገር እንዳለ አስተዋልክ? ኤልያስ ለአክዓብ “የከባድ ዝናብ ድምፅ ይሰማል” ብሎት እንደነበር አስታውስ። ነቢዩ የዝናብ ደመና ባልታየበት ሁኔታ እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ሊናገር ቻለ?
ኤልያስ፣ ይሖዋ የገባውን ቃል ያውቃል። የይሖዋ ነቢይና ወኪል እንደመሆኑ መጠን አምላኩ ቃሉን እንደሚጠብቅ እርግጠኛ ነበር። ኤልያስ በይሖዋ ይተማመን ስለነበር ከባድ ዝናብ መጣል የጀመረ ያህል ተሰምቶት ነበር። ይህ ታሪክ፣ መጽሐፍ ቅዱስ “የማይታየውንም እንዳየው አድርጎ በመቊጠር በሐሳቡ ጸና” በማለት ስለ ሙሴ የተናገረውን አባባል ያስታውሰን ይሆናል። አምላክ ለአንተ ይህን ያህል እውን ነው? ይሖዋ፣ በእሱና በገባቸው ተስፋዎች ላይ እንዲህ ያለ እምነት እንድንጥል የሚያደርግ በቂ ማስረጃ ሰጥቶናል።—ዕብራውያን 11:1, 27
-