-
በንቃትና በትዕግሥት ተጠባብቋልመጠበቂያ ግንብ—2008 | ሚያዝያ 1
-
-
የይሖዋ ነቢይ፣ አክዓብ የሄደበትን መንገድ ተከትሎ መጓዝ ጀመረ። ረጅም፣ በጨለማ የተዋጠና የጨቀየ መንገድ ይጠብቀዋል። ሆኖም በመቀጠል አንድ ያልተለመደ ነገር ተከሰተ።
“የእግዚአብሔርም ኀይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን ከፍ አድርጎ በቀበቶው ካጠበቀ በኋላ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ በአክዓብ ፊት ሮጠ።” (ቁጥር 46) ከዚህ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው ‘የእግዚአብሔር ኀይል’ በኤልያስ ላይ ከሰው አቅም በላይ በሆነ መንገድ እየሠራ ነበር። ኢይዝራኤል የምትገኘው 30 ኪሎ ሜትር ገደማ ላይ ሲሆን ኤልያስ ደግሞ ዕድሜው ገፍቷል።e ይህ ነቢይ ረጅሙን መጎናጸፊያ ለብሶ፣ እግሮቹን እንደ ልብ ለማንሳት እንዲያመቸው ልብሶቹን ሰብሰብ አድርጎ ወገቡ ላይ በቀበቶ ሸብ በማድረግ በጨቀየው መንገድ ላይ ሲሮጥ በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። የቤተ መንግሥቱ ሠረገላ ላይ ለመድረስ አልፎ ተርፎም ቀድሞት ለመሄድ በከፍተኛ ፍጥነት እየሮጠ ነው!
ይህ ለኤልያስ እንዴት ያለ በረከት ነበር! እንዲህ የመሰለ ምናልባትም በወጣትነት ጊዜው ተሰምቶት የማያውቀው ዓይነት ኃይል፣ ጥንካሬና ብርታት ሲሰማው ምን ያህል ተደስቶ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ይህ ሁኔታ ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች ወደፊት ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ፍጹም የሆነ ጤንነትና ብርታት እንደሚያገኙ ዋስትና የሚሰጡትን ትንቢቶች ሳያስታውሰን አልቀረም። (ኢሳይያስ 35:6፤ ሉቃስ 23:43) ኤልያስ በዚያ በጨቀየ መንገድ ላይ ሲሮጥ፣ ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነውን የአባቱን የይሖዋን ሞገስ እንዳገኘ ተገንዝቦ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም!
-
-
በንቃትና በትዕግሥት ተጠባብቋልመጠበቂያ ግንብ—2008 | ሚያዝያ 1
-
-
e ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ይሖዋ ኤልሳዕን እንዲያሠለጥነው ለኤልያስ ኃላፊነት ሰጠው። ኤልሳዕ ከዚህ ቀደም “የኤልያስን እጅ ያስታጥብ” እንደነበር ተጠቅሷል። (2 ነገሥት 3:11) ከሁኔታው መረዳት እንደሚቻለው ኤልሳዕ፣ አረጋዊውን ኤልያስን ለመርዳት የሚችለውን ሁሉ በማድረግ አገልጋዩ ሆኖ ሠርቷል።
-