የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከፍተኛ ወሮታ ያስገኘ ጉብኝት
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሐምሌ 1
    • የይሖዋን ፈቃድ ፈጽመዋል

      ከፍተኛ ወሮታ ያስገኘ ጉብኝት

      ንግሥቲቱ ከሳባ ወደ ኢየሩሳሌም ያደረገችው ጉዞ አድካሚ ሳይሆንባት አልቀረም። በተንደላቀቀ ሁኔታ መኖር የለመደች ናት። አሁን ግን በአብዛኛው እንደ እሳት በሚያቃጥለው በረሃ በግመል ፍጥነት የ2,400 ኪሎ ሜትር ጉዞ እያደረገች ነው። በአንድ ግምት መሠረት ያደረገችውን ጉዞ ለማጠናቀቅ ወደ 75 ቀናት ገደማ ሊፈጅባት ይችላል፤ ይህ ደግሞ ለመሄድ ወይም ለመመለስ ብቻ የሚፈጅባት ጊዜ ነው!a

      ይህች ባለጸጋ ንግሥት በሳባ የሚገኘውን ምቹ መኖሪያዋን ትታ እንዲህ ዓይነት አድካሚ ጉዞ ያደረገችው ለምን ነበር?

      ጉጉት የሚቀሰቅስ ወሬ

      የሳባ ንግሥት ወደ ኢየሩሳሌም የመጣችው ‘እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ከሰማች’ በኋላ ነበር። (1 ነገሥት 10:​1 የ1980 ትርጉም) በትክክል ንግሥቲቱ የሰማችው ነገር ምን እንደሆነ አልተጻፈም። ሆኖም ይሖዋ ሰሎሞንን ወደር የሌለው ጥበብ፣ ሀብትና ክብር በመስጠት ባርኮት እንደነበር እናውቃለን። (2 ዜና መዋዕል 1:​11, 12) ንግሥቲቱ ስለዚህ ነገር እንዴት ልታውቅ ቻለች? ሳባ የንግድ ማዕከል ስለነበረች ንግሥቲቱ ወደ አገሯ በሚመጡ ነጋዴዎች አማካኝነት ስለ ሰሎሞን ዝና ሰምታ ሊሆን ይችላል። ከእነዚህ አንዳንዶቹ ሰሎሞን ከፍተኛ የንግድ ግንኙነት ያደርግባት ወደነበረው ወደ ኦፊር ምድር የሚጓዙ ሊሆኑ ይችላሉ።​—⁠1 ነገሥት 9:​26-28

  • ከፍተኛ ወሮታ ያስገኘ ጉብኝት
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሐምሌ 1
    • ሆኖም ንግሥቲቱ ‘ከይሖዋ ስም ጋር በተያያዘ’ የሚነገረውን የሰሎሞን ዝና እንደሰማች ልብ በል። በመሆኑም ይህ ለንግድ ብቻ ተብሎ የተደረገ ጉዞ አልነበረም። ከሁኔታዎቹ ለመረዳት እንደሚቻለው ንግሥቲቱ በአንደኛ ደረጃ የመጣችበት ዓላማ የሰሎሞንን ጥበብ፣ አልፎ ተርፎም ስለ አምላኩ ስለ ይሖዋ የሆነ ነገር ለማወቅ ፈልጋ ሳይሆን አይቀርም። የይሖዋ አምላኪዎች የሆኑት የሴም ወይም የካም ዝርያ ልትሆን ስለምትችል ቅድመ አያቶቿ ይከተሉት ስለነበረው ሃይማኖት የማወቅ ጉጉት አድሮባት ሊሆን ይችላል።

      አመራማሪ ጥያቄዎች፣ አርኪ መልሶች

      ንግሥቲቱ ከሰሎሞን ጋር በተገናኘች ጊዜ “አመራማሪ በሆኑ ጥያቄዎች” ትፈትነው ጀመር። (1 ነገሥት 10:​1 NW) እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “እንቆቅልሽ” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። ሆኖም እንዲህ ሲባል ንግሥቲቱ ሰሎሞንን በአልባሌ ቀልዶች አጥምዳዋለች ማለት አይደለም። በመዝሙር 49:​4 NW ላይ ኃጢአትን፣ ሞትንና ቤዛን የሚመለከቱ አሳሳቢ ጥያቄዎችን ለመግለጽ ይኸው የዕብራይስጥ ቃል የተሠራበት መሆኑ ትኩረት የሚስብ ነው። ስለዚህ የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን የማስተዋል ጥልቀት የሚፈትኑ ከበድ ያሉ ጉዳዮችን ሳታወያየው አትቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ “በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው” ሲል ይገልጻል። በአጸፋው ደግሞ ሰሎሞን “የጠየቀችውን ሁሉ ፈታላት፤ ሊፈታላት ያልቻለውና ከንጉሡ የተሰወረ ነገር አልነበረም።”​—⁠1 ነገሥት 10:​2, 3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ