የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በሰራፕታ የነበረችው መበለት ያሳየችው እምነት ክሷታል
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | የካቲት 15
    • ይሖዋ ክፉ በነበረው በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብ ግዛት ረጅም ጊዜ የዘለቀ ድርቅ እንዲከሰት አድርጎ ነበር። ኤልያስ ድርቁ እንደሚከሰት ካወጀ በኋላ አምላክ፣ ኤልያስን ከአክዓብ የሸሸገው ሲሆን ቁራዎች እንጀራና ሥጋ እያመጡ በተአምር እንዲመግቡት አድርጎ ነበር። ከዚያም ይሖዋ ኤልያስን እንዲህ አለው፦ “ተነሥና ሲዶና ውስጥ ወዳለችው ወደ ሰራፕታ ሄደህ ተቀመጥ፤ በዚያም አንዲት መበለት እንድትመግብህ አዝዣለሁ።”—1 ነገ. 17:1-9

  • በሰራፕታ የነበረችው መበለት ያሳየችው እምነት ክሷታል
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | የካቲት 15
    • ይህች መበለት ኤልያስ አምላክን የሚፈራ እስራኤላዊ መሆኑን ተገንዝባለች። “አምላክህን ሕያው ይሖዋን” ብላ መናገሯ ይህን ይጠቁማል። የእስራኤል አምላክ ስለሆነው ስለ ይሖዋ የተወሰነ እውቀት ያላት ቢመስልም ይሖዋን “አምላኬ” ብላ ለመጥራት የሚያስችላት እውቀት ግን አልነበራትም። ይህች ሴት ትኖር የነበረው በሰራፕታ ሲሆን ከተማዋ ደግሞ የፊንቄያውያን ከተማ የሆነችው የሲዶና ክፍል ወይም በሥሯ የምትተዳደር ከተማ የነበረች ይመስላል። ሰራፕታ የበአል አምላኪዎች የሚኖሩባት ከተማ ሳትሆን አትቀርም። ያም ሆኖ ይሖዋ በዚህች መበለት ውስጥ ያየው አንድ ልዩ ነገር አለ።

      በሰራፕታ የምትኖረው ይህች ድሃ መበለት በጣዖት አምላኪዎች የተከበበች ብትሆንም በይሖዋ ላይ እምነት ነበራት። ይሖዋ ኤልያስን ወደ እሷ የላከው ለሴትየዋም ሆነ ለነቢዩ ጥቅም ብሎ ነው። ከዚህ ታሪክ አንድ ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን።

      በሰራፕታ የሚኖሩት የበአል አምላኪዎች በሙሉ ምግባረ ብልሹዎች አልነበሩም። ይሖዋ ኤልያስን ወደዚህች መበለት መላኩ እሱን የማያገለግሉትን ሆኖም ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች እንደሚመለከት ያስገነዝበናል። በእርግጥም “ከየትኛውም ብሔር ቢሆን [አምላክን] የሚፈራና የጽድቅ ሥራ የሚሠራ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”—ሥራ 10:35

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ