የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለዘመናችን የሚሆን መልእክት ያስተላለፈ ጥንታዊ ነቢይ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 7. በኢሳይያስ ዘመን በይሁዳ የነበረው ሁኔታ ምን እንደሚመስል ግለጽ።

      7 ኢሳይያስና ቤተሰቡ የኖሩት በይሁዳ ታሪክ ሥርዓት አልበኝነት በነገሠበት ዘመን ነበር። ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና በጉቦ መፍረድ በእጅጉ ተስፋፍቶ የነበረ ሲሆን ግብዝነት የኅብረተሰቡን ሃይማኖታዊ መዋቅር አፍረክርኮት ነበር። የኮረብታዎቹ አናት ለሐሰት አማልክት በቆሙ መሠዊያዎች ተሸፍኖ ነበር። አንዳንዶቹ ነገሥታት ሳይቀሩ አረማዊ አምልኮዎችን አራምደዋል። ለምሳሌ አካዝ በተገዢዎቹ መካከል የነበረውን የጣዖት አምልኮ በቸልታ ከመመልከትም አልፎ ለከነዓናውያኑ አምላክ ለሞሎክ መሥዋዕት አድርጎ ‘ልጁን በእሳት በማሳለፍ’ ራሱም ጭምር የዚህ አምልኮ ተሳታፊ ሆኗል።b (2 ነገሥት 16:​3, 4፤ 2 ዜና መዋዕል 28:​3, 4) እንግዲህ ይህ ሁሉ የተፈጸመው ከይሖዋ ጋር የቃል ኪዳን ዝምድና በነበረው ሕዝብ መካከል ነበር!​—⁠ዘጸአት 19:​5-8

  • ለዘመናችን የሚሆን መልእክት ያስተላለፈ ጥንታዊ ነቢይ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • b አንዳንዶች ‘በእሳት ማሳለፍ’ የሚለው አባባል የሚያመለክተው አንድን የመንጻት ሥርዓት ነው ይላሉ። ይሁንና ከጥቅሱ አገባብ መረዳት እንደሚቻለው ይህ ሐረግ የሚናገረው ቃል በቃል ስለቀረበ መሥዋዕት ነው። በከነዓናውያንና ከሃዲ በነበሩ እስራኤላውያን ዘንድ ልጆችን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብ የተለመደ ነገር መሆኑ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም።​—⁠ዘዳግም 12:​31፤ መዝሙር 106:​37, 38

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ