የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ንጉሡ ያሳየው እምነት ተካሰ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 4, 5. (ሀ) ሕዝቅያስ ከአሦር ቀንበር ነፃ መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው? (ለ) ሰናክሬም በይሁዳ ላይ የወሰደው ወታደራዊ እርምጃ ምንድን ነው? ሕዝቅያስስ በኢየሩሳሌም ላይ ሊሰነዘር የሚችለውን ቅጽበታዊ ጥቃት ለማስቀረት ምን እርምጃ ወስዷል? (ሐ) ሕዝቅያስ ኢየሩሳሌምን ከአሦራውያን ለመከላከል ዝግጅት ያደረገው እንዴት ነው?

      4 ኢየሩሳሌም ከባድ ፈተናዎች ይጠብቋታል። ሕዝቅያስ ከሃዲ የነበረው አባቱ አካዝ ከአሦራውያን ጋር ገብቶት የነበረውን ኅብረት አፍርሷል። ከዚህም በላይ የአሦራውያን አጋር የነበሩትን ፍልስጥኤማውያንንም መትቷል። (2 ነገሥት 18:​7, 8) ይህም የአሦሩን ንጉሥ አስቆጥቶት ነበር። በመሆኑም እንዲህ የሚል እናነባለን:- “እንዲህም ሆነ፤ በንጉሡ በሕዝቅያስ በአሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰዳቸው።” (ኢሳይያስ 36:​1) ሕዝቅያስ ምሕረት የለሽ የሆነው የአሦር ሠራዊት ከሚሰነዝረው ቅጽበታዊ ጥቃት ኢየሩሳሌምን ለመከላከል በማሰብ ይመስላል ለሰናክሬም ከፍተኛ መጠን ያለው ግብር ማለትም 300 መክሊት ብርና 30 መክሊት ወርቅ ለመክፈል ተስማማ።a​—⁠2 ነገሥት 18:​14

      5 በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ውስጥ ይህን ግብር ለመስጠት የሚያስችል በቂ መጠን ያለው ወርቅና ብር ስላልነበረ ሕዝቅያስ በቤተ መቅደሱ ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ አሰባስቧል። በወርቅ በተለበጠው የቤተ መቅደስ በር ላይ ሳይቀር የነበረውን ወርቅ አስቆርጦ ለሰናክሬም ልኳል። ይህ አሦራውያንን አርክቷቸዋል። ሆኖም ለጊዜው ብቻ ነበር። (2 ነገሥት 18:​15, 16) አሦራውያን ብዙም ሳይቆዩ እንደገና ፊታቸውን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመልሱ ሕዝቅያስ ተገንዝቦ እንደነበር ከሁኔታዎቹ ለመረዳት ይቻላል። በመሆኑም አንዳንድ ዝግጅቶች መደረግ ነበረባቸው። ሕዝቡ ወራሪው የአሦር ኃይል ውኃ እንዳያገኝ ውኃ ያለባቸውን ቦታዎች ሁሉ ደፈነ። በተጨማሪም ሕዝቅያስ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ከማጠናከሩም ሌላ ‘ተወንጫፊ መሣሪያዎችንና ጋሻዎችን’ ጨምሮ የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤቶችን አስገነባ።​—⁠2 ዜና መዋዕል 32:​4, 5 NW

  • ንጉሡ ያሳየው እምነት ተካሰ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • a ዛሬ ባለው የዋጋ ተመን መሠረት ከ9.5 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ያወጣል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ