የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ጸሎትን የሚሰማ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥቅምት 1
    • በእርግጥ ይሖዋ አምላክ ታማኝ አምላኪዎቹ የሚያቀርቡትን ልባዊ ጸሎት ይሰማል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያቤጽ ስለሚባል እምብዛም የማይታወቅ ሰው ተመዝግቦ የሚገኘው ታሪክ በእርግጥም ይሖዋ ‘ጸሎትን የሚሰማ’ አምላክ መሆኑን ያሳያል። (መዝሙር 65:2) ይህ አጭር ታሪክ የሚገኘው በማንጠብቀው ቦታ ይኸውም በአንደኛ ዜና መዋዕል መጽሐፍ መግቢያ ላይ ባለው የዘር ሐረግ ዝርዝር ውስጥ ነው። እስቲ 1 ዜና መዋዕል 4:9, 10⁠ን አብረን እንመርምር።

      ስለ ያቤጽ የምናውቀው ነገር ቢኖር በእነዚህ ሁለት ቁጥሮች ላይ የሰፈረውን ሐሳብ ብቻ ነው። ቁጥር 9 “እናቱም ‘በጣር የወለድሁት’ ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው” ይላል።a እንዲህ ያለ ስም ለልጇ ያወጣችለት ለምንድን ነው? እሱን በምትወልድበት ወቅት ከወትሮው በተለየ ምጥ ጠንቶባት ይሆን? ምናልባትም መበለት ስለነበረች ይሆን? ከሆነ ልጇን ስትወልድ ባሏ አጠገቧ አለመሆኑ አስጨንቋት ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ምክንያቱን አይገልጽም። ያም ሆነ ይህ እናቱ ከጊዜ በኋላ በዚህ ልጅ እንድትኮራ የሚያደርጋት ምክንያት ይኖራታል። የያቤጽ ወንድሞችና እህቶች ጥሩ ሰዎች የነበሩ ሊሆን ቢችልም እሱ ግን “ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ።”

  • ‘ጸሎትን የሚሰማ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥቅምት 1
    • a ያቤጽ የሚለው ስም “ሥቃይ” የሚል ትርጉም ካለው ቃል የተገኘ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ