የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ጸሎትን የሚሰማ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥቅምት 1
    • በእርግጥ ይሖዋ አምላክ ታማኝ አምላኪዎቹ የሚያቀርቡትን ልባዊ ጸሎት ይሰማል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያቤጽ ስለሚባል እምብዛም የማይታወቅ ሰው ተመዝግቦ የሚገኘው ታሪክ በእርግጥም ይሖዋ ‘ጸሎትን የሚሰማ’ አምላክ መሆኑን ያሳያል። (መዝሙር 65:2) ይህ አጭር ታሪክ የሚገኘው በማንጠብቀው ቦታ ይኸውም በአንደኛ ዜና መዋዕል መጽሐፍ መግቢያ ላይ ባለው የዘር ሐረግ ዝርዝር ውስጥ ነው። እስቲ 1 ዜና መዋዕል 4:9, 10⁠ን አብረን እንመርምር።

  • ‘ጸሎትን የሚሰማ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥቅምት 1
    • ያቤጽ የጸሎት ሰው ነበር። ያቤጽ ጸሎቱን የጀመረው የአምላክን በረከት ለማግኘት በመለመን ነው። ከዚያም በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት እንዳለው የሚያሳዩ ሦስት ልመናዎችን አቀረበ።

      በመጀመሪያ “ግዛቴንም እንድታሰፋ እለምንሃለሁ” ሲል አምላክን ተማጽኗል። (ቁጥር 10) ይህ የተከበረ ሰው የባልንጀራውን መሬት የሚመኝ ስግብግብ አልነበረም። ከልቡ ያቀረበው ይህ ልመና ይዞታን ሳይሆን ሰዎችን የሚመለከት ሊሆን ይችላል። ምናልባት እውነተኛውን አምላክ የሚያመልኩ በርካታ ሰዎችን መያዝ የሚችል ይዞታ እንዲኖረው ግዛቱ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲሰፋለት መጠየቁ ሊሆን ይችላል።b

      ቀጥሎም ያቤጽ የአምላክ “እጅ” ከእሱ ጋር እንዲሆን ልመና አቅርቧል። የአምላክ እጅ ሲባል በሥራ ላይ የዋለውን ኃይሉን ያመለክታል፤ ይሖዋ አገልጋዮቹን ለመርዳት በዚህ ኃይል ይጠቀማል። (1 ዜና መዋዕል 29:12) ያቤጽ የለመነውን ነገር ለማግኘት ዘወር ያለው ወደ አምላክ ሲሆን ይሖዋም በእሱ ላይ እምነት ያላቸውን ሰዎች ፍላጎት ለማሟላት እጁ አጭር አይደለም።—ኢሳይያስ 59:1

      በሦስተኛ ደረጃ ያቤጽ “እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ” (የ1954 ትርጉም) በማለት ጸልዮአል። “እንዳያሳዝነኝ” የሚለው አገላለጽ ያቤጽ የጸለየው መከራ እንዳይደርስበት ሳይሆን ክፋት በሚያስከትለው ነገር እንዳያዝን ወይም እንዳይሸነፍ መሆኑን ሊያመለክት ይችላል።

      ያቤጽ ያቀረበው ጸሎት ከእውነተኛው አምልኮ ጋር የተያያዙ ነገሮች እንደሚያሳስቡት እንዲሁም ጸሎት ሰሚ በሆነው አምላክ ላይ እምነት እንዳለው በግልጽ ያሳያል። ታዲያ ይሖዋ ምን መልስ ሰጠው? ይህ አጭር ዘገባ ታሪኩን የሚቋጨው “እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው” በማለት ነው።

      ጸሎት ሰሚ የሆነው አምላክ ዛሬም ቢሆን አልተለወጠም። የሚያመልኩት ሰዎች በሚያቀርቡት ጸሎት ይደሰታል። በእሱ ላይ እምነት የሚያሳድሩ ሁሉ እንደሚከተለው ያለ መተማመን ሊኖራቸው ይችላል፦ “የምንጠይቀው ነገር ምንም ይሁን ምን ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እስከለመንን ድረስ ይሰማናል።”—1 ዮሐንስ 5:14

  • ‘ጸሎትን የሚሰማ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥቅምት 1
    • b ታርገም የሚባለው አይሁዶች ያዘጋጁት ነፃ የቅዱሳን መጻሕፍት ትርጉም የያቤጽን ጸሎት እንዲህ በማለት አስቀምጦታል፦ “ብዙ ልጆች በመስጠት ባርከኝ፤ ደቀ መዛሙርት በመስጠት ግዛቴን አስፋልኝ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ