የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w04 1/1 ገጽ 32
  • አምላክ ስለ እኛ ያስባል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ስለ እኛ ያስባል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
w04 1/1 ገጽ 32

አምላክ ስለ እኛ ያስባል?

ከቤተሰብህ፣ ከጤንነትህና ከሥራህ ወይም ካሉብህ ሌሎች ከባድ ኃላፊነቶች ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙህ ችግሮች የስሜት ጫና እንዳስከተሉብህ ይሰማሃል? ብዙ ሰዎች እንደዚህ ይሰማቸዋል። ደግሞስ ዛሬ የፍትሕ መጓደል፣ ወንጀልና ዓመጽ ያልነካው ማን አለ? በእርግጥም ሁኔታው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ነው:- “ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ [ይኖራል]።” (ሮሜ 8:22) ብዙ ሰዎች ‘አምላክ ስለ እኛ ያስባል? እኛን ለመርዳት እርምጃ ይወስድ ይሆን?’ ብለው መጠየቃቸው ምንም አያስገርምም።

ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን ለአምላክ ባቀረበው ጸሎት ላይ “አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ልብ ታውቃለህና” ብሏል። ሰሎሞን አምላክ እኛን ከማወቅም በላይ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብልን እርግጠኛ ነበር። አምላክ ‘በሰማይ ሆኖ እንዲሰማ’ እንዲሁም እርሱን የሚፈራ እያንዳንዱ ግለሰብ “ሕመሙንና ኀዘኑን” በጸሎት ቢያቀርብ ሰምቶ እንዲመልስ ለምኖታል።—2 ዜና መዋዕል 6:29, 30

ዛሬም ቢሆን ይሖዋ አምላክ ስለ እኛ የሚያስብ ከመሆኑም በላይ ወደ እርሱ እንድንጸልይ ያበረታታናል። (መዝሙር 50:15) ከፈቃዱ ጋር ለሚስማሙ ከልብ የመነጩ ጸሎቶች ምላሽ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። (መዝሙር 55:16, 22፤ ሉቃስ 11:5-13፤ 2 ቆሮንቶስ 4:7) በእርግጥም ይሖዋ ‘ማንም ሰው ወይም ሕዝቦቹ ጸሎትና ልመና ቢያደርጉ’ ይሰማል። በመሆኑም በአምላክ ከታመንን፣ እንዲረዳን ከጸለይንና ወደ እርሱ ከቀረብን ፍቅራዊ እንክብካቤውንና መመሪያውን እናገኛለን። (ምሳሌ 3:5, 6) የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ያዕቆብ “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል” የሚል ዋስትና ሰጥቶናል።—ያዕቆብ 4:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ