የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘የድካማችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ነሐሴ 15
    • አሳ ከጦርነቱ ሲመለስ ከአዛርያስ ጋር ተገናኘ። ይህ ነቢይ ለአሳ እንደሚከተለው በማለት ማበረታቻ እንዲሁም ማስጠንቀቂያ ሰጠው፦ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር [“ከይሖዋ፣” NW] ጋር ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተውት ግን፣ ይተዋችኋል። . . . የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።”​—2 ዜና 15:1, 2, 7

      ይህ ሐሳብ የእኛንም እምነት ሊያጠናክር ይችላል። ይሖዋን በታማኝነት እስካገለገልነው ድረስ ምንጊዜም ከእኛ ጋር እንደሚሆን ዋስትና ይሰጠናል። ይሖዋ ለእርዳታ ወደ እሱ ከጮኽን እንደሚሰማን እርግጠኞች መሆን እንችላለን። አዛርያስ “በርቱ” በማለት ተናግሯል። ብዙ ጊዜ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ብርቱ ወይም ደፋር መሆን ይጠይቃል። ይሁን እንጂ ይህን ማድረግ የምንችለው በይሖዋ እርዳታ እንደሆነ እናውቃለን።

  • ‘የድካማችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ነሐሴ 15
    • ነቢዩ አዛርያስ የተናገረው ነገር ማስጠንቀቂያም ያዘለ ነበር። “[አምላክን] ብትተውት ግን፣ ይተዋችኋል” ብሎት ነበር። ማናችንም ብንሆን እንዲህ ያለ ነገር እንዲደርስብን አንፈልግም፤ ምክንያቱም መዘዙ የከፋ ነው። (2 ጴጥ. 2:20-22) ቅዱሳን መጻሕፍት ይሖዋ ይህን መልእክት ለአሳ የላከበትን ምክንያት አይነግሩንም፤ ያም ሆነ ይህ ንጉሡ ማስጠንቀቂያውን ችላ ብሎ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ