የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አስቀድሞ ለተጻፉት ነገሮች ትኩረት ትሰጣላችሁ?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | መጋቢት
    • 12 የሕዝቅያስ ልብ እንዲታበይ ያደረገው ምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አይገልጽም። ይህ የሆነው በአሦራውያን ላይ ድል ስለተጎናጸፈ አሊያም አምላክ በተአምራዊ መንገድ ስለፈወሰው ይሆን? ወይስ “እጅግ ብዙ ሀብት” እና “ታላቅ ክብር” ስላገኘ ነው? ምክንያቱ ምንም ሆነ ምን ሕዝቅያስ ስለታበየ “ለተደረገለት መልካም ነገር አድናቆት ሳያሳይ [ቀርቷል]።” ይህ ምንኛ የሚያሳዝን ነው! ሕዝቅያስ አምላክን በሙሉ ልቡ ያገለገለ ቢሆንም ይሖዋን ያሳዘነበት ጊዜ ነበር። በኋላ ላይ ግን ሕዝቅያስ “ራሱን ዝቅ አደረገ።” በመሆኑም እሱም ሆነ ሕዝቡ የይሖዋ ቁጣ አልመጣባቸውም።—2 ዜና 32:25-27፤ መዝ. 138:6

  • አስቀድሞ ለተጻፉት ነገሮች ትኩረት ትሰጣላችሁ?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | መጋቢት
    • 14 ሌሎች ሲያመሰግኑን ኢየሱስ የሰጠውን የሚከተለውን ምክር ተግባራዊ ማድረጋችን ጠቃሚ ነው፦ “እናንተም የተሰጣችሁን ሥራ ሁሉ ባከናወናችሁ ጊዜ ‘ምንም የማንጠቅም ባሪያዎች ነን። ያደረግነው ልናደርገው የሚገባንን ነገር ነው’ በሉ።” (ሉቃስ 17:10) በዚህ ረገድም ሕዝቅያስ ከሠራው ስህተት ትምህርት ማግኘት እንችላለን። ሕዝቅያስ ልቡ ስለታበየ “ለተደረገለት መልካም ነገር አድናቆት ሳያሳይ [ቀርቷል]።” ይሖዋ ባደረገልን በርካታ መልካም ነገሮች ላይ ማሰላሰላችን እሱ የሚጠላውን ዝንባሌ እንድናስወግድ ይረዳናል። ስለ ይሖዋና ስላደረገልን ነገሮች መናገራችንም ጠቃሚ ነው። ደግሞም ቅዱሳን መጻሕፍትን እንዲሁም ለሕዝቡ ድጋፍ የሚያደርገውን ቅዱስ መንፈሱን የሰጠን እሱ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ