የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለች
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ጥቅምት 1
    • ሐማ የሚባል አንድ ሰው በጠረክሲስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ቦታ እያገኘ መጣ። ንጉሡ ለሐማ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ በመስጠት ዋነኛ አማካሪውና በግዛቱ ውስጥ ሁለተኛ ሰው አድርጎ ሾመው። ከዚህም በላይ ንጉሡ፣ ሰዎች ለዚህ ባለሥልጣን እንዲሰግዱለት ትእዛዝ አስተላለፈ። (አስቴር 3:1-4) ይህ ሕግ በመርዶክዮስ ላይ ችግር የሚፈጥር ነበር። ንጉሡን መታዘዝ እንዳለበት ያምናል፤ ይሁንና ይህን ለማድረግ ሲል የአምላክን ሕግ መጣስ እንደሌለበትም ያውቃል። ሐማ “አጋጋዊ” መሆኑ መረሳት የሌለበት ነገር ነው። ይህ ሲባል ሐማ የአጋግ ዝርያ ነው ማለት ነው፤ አጋግ ደግሞ የአምላክ ነቢይ የነበረው ሳሙኤል የገደለው የአማሌቃውያን ንጉሥ ነበር። (1 ሳሙኤል 15:33) አማሌቃውያን እጅግ ክፉ ከመሆናቸው የተነሳ የይሖዋና የእስራኤላውያን ጠላቶች ሆነው ነበር። አማሌቃውያን በብሔር ደረጃ አምላክ ጥፋት የወሰነባቸው ሕዝቦች ነበሩ።b (ዘዳግም 25:19) ታዲያ አንድ ታማኝ አይሁዳዊ በቤተ መንግሥት ውስጥ ሥልጣን ላለው አንድ አማሌቃዊ እንዴት ሊሰግድ ይችላል? መርዶክዮስ ይህን ሊያደርግ አይችልም። ደግሞም ከአቋሙ ፍንክች አላለም። ዛሬም ቢሆን አምላክን በታማኝነት የሚያገለግሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች “ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል” የሚለውን መመሪያ በጥብቅ ለመከተል ሲሉ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለዋል።​—የሐዋርያት ሥራ 5:29

  • ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለች
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ጥቅምት 1
    • b ከአማሌቃውያን መካከል “የቀሩት” በንጉሥ ሕዝቅያስ የግዛት ዘመን ተደምስሰው ስለነበር ሐማ በሕይወት ተርፈው ከነበሩት ጥቂት አማሌቃውያን ውስጥ አንዱ መሆን አለበት።​—1 ዜና መዋዕል 4:43

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ