የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ንጹሕ አቋሜን አላጎድፍም!”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • ያም ቢሆን ኢዮብ ጠንካራ እምነት ያለው ሰው ነበር። ከጓደኞቹ ጋር ባደረገው ክርክር ላይ የጠቀሰው አብዛኛው ሐሳብ ለዚህ ማስረጃ ይሆናል፤ የተናገራቸው ቃላት ዛሬም ድረስ ትክክል፣ ማራኪና አበረታች ናቸው። አስደናቂ ስለሆኑት የይሖዋ ፍጥረታት በተናገረበት ወቅት አምላክ ካልገለጠለት በቀር ማንም ሰው በሌላ መንገድ ሊያውቀው የማይችለውን ነገር ተናግሯል። ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋ ‘ምድርን ያለምንም ነገር እንዳንጠለጠለ’ ገልጿል፤ የሳይንስ ሊቃውንት ይህን የደረሱበት ከበርካታ መቶ ዘመናት በኋላ ነው።b (ኢዮብ 26:7) ኢዮብ ስለ ወደፊት ተስፋው የተናገረው ሐሳብም እንደ ሌሎች የእምነት አባቶች ታላቅ እምነት እንዳለው የሚያሳይ ነው። ቢሞት እንኳ አምላክ እንደሚያስታውሰው፣ እንደሚናፍቀው አልፎ ተርፎም ከሞት እንደሚያስነሳው ያምን ነበር።—ኢዮብ 14:13-15፤ ዕብራውያን 11:17-19, 35

  • “ንጹሕ አቋሜን አላጎድፍም!”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • b የሳይንስ ሊቃውንት ምድር ያለምንም ድጋፍ እንደተንጠለጠለች የሚገልጽ ንድፈ ሐሳብ ማቅረብ የጀመሩት ከ3,000 ዓመት ገደማ በኋላ ሳይሆን አይቀርም። አብዛኞቹ ሰዎች ኢዮብ የተናገረውን ሐሳብ እውነተኝነት መቀበል የጀመሩት ደግሞ ምድርን ከሕዋ ላይ ፎቶግራፍ ማንሳት ከተጀመረ በኋላ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ