የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአምላክን ድንቅ ሥራዎች በትኩረት ተመልከቱ
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ሚያዝያ 15
    • 3. በኢዮብ 38:​22, 23, 25-29 ላይ ተመዝግቦ በሚገኘው መሠረት አምላክ ስለ ምን ነገሮች ጠይቋል?

      3 በአንድ ወቅት አምላክ ኢዮብን እንዲህ በማለት ጠይቆት ነበር:- “በውኑ ወደ በረዶው ቤተ መዛግብት ገብተሃልን? የበረዶውንስ ቅንጣት ቤተ መዛግብት አይተሃልን? ይኸውም ለመከራ ጊዜ ለሰልፍና ለጦርነት ቀን የጠበቅሁት ነው።” በብዙ የምድር ክፍል በረዶ የተለመደ ነገር ነው። አምላክ እንዲህ በማለት ይቀጥላል:- “ሣሩንም እንዲያበቅል፣ ማንም በሌለባት ምድር ላይ፣ ሰውም በሌለባት ምድረ በዳ ላይ ዝናብን ያዘንብ ዘንድ፣ ለፈሳሹ ውኃ መንዶልዶያውን፣ ወይስ ለሚያንጐደጉድ መብረቅ መንገድን ያበጀ ማን ነው? በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው? በረዶስ ከማን ማኅፀን ወጣ? የሰማዩንስ አመዳይ ማን ወለደው?”​—⁠ኢዮብ 38:​22, 23, 25-29

  • የአምላክን ድንቅ ሥራዎች በትኩረት ተመልከቱ
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ሚያዝያ 15
    • 7. የሰው ልጅ ስለ ዝናብ ያለው እውቀት ምን ያህል ነው?

      7 ስለ ዝናብስ ምን ሊባል ይችላል? አምላክ ኢዮብን “በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው?” በማለት ጠይቆት ነበር። ቀደም ሲል የተጠቀሰው የሳይንስ ኢንሳይክሎፔዲያ እንዲህ ይላል:- “የከባቢ አየር እንቅስቃሴ እጅግ የተወሳሰበ በመሆኑና በአየር ውስጥ ያለው የተንና የሌሎች ቅንጣቶች ይዘት እጅግ የተለያየ በመሆኑ ደመናና ጠል ስለሚፈጠርበት መንገድ ዘርዘር ያለና አጠቃላይ የሆነ ንድፈ ሐሳብ መስጠት ፈጽሞ የማይቻል ይመስላል።” በአጭሩ ሳይንቲስቶች ስለ ዝናብ ዝርዝር ንድፈ ሐሳቦችን ቢያቀርቡም የተሟላ ማብራሪያ መስጠት ግን አልቻሉም። ቢሆንም ዝናብ ምድራችንን በማጠጣት እጽዋት እንዲለመልሙ ስለሚያደርግ በሕይወት ለመኖርና ለመደሰት እንደቻልን ታውቃለህ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ