-
‘ወፎችን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ’ንቁ!—2014 | ነሐሴ
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ትምህርቶችን ለማስተላለፍ ወፎችን ብዙ ጊዜ ይጠቅሳል። ለምሳሌ ያህል፣ አምላክ ሰጎን የምትባለውን አስገራሚ ፍጥነት ያላት ወፍ አስመልክቶ ለኢዮብ እንዲህ ብሎት ነበር፦ “[ሰጎን] ለመሸምጠጥም ክንፎቿን ስትዘረጋ፣ በፈረስና በጋላቢው ትሥቃለች።”a (ኢዮብ 39:13, 18) በተጨማሪም አምላክ “ጭልፊት የሚበረው . . . በአንተ ጥበብ ነውን? ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው . . . በአንተ ትእዛዝ ነውን?” የሚል ጥያቄ ለኢዮብ አቅርቦለት ነበር። (ኢዮብ 39:26, 27) አምላክ ለማስተላለፍ የፈለገው ትምህርት ምንድን ነው? ወፎች የእኛ እርዳታ ሳያስፈልጋቸው አስደናቂ ነገሮችን ያከናውናሉ። ስለዚህ እነዚህ ወፎች ያላቸው አስደናቂ ችሎታ የአምላክን ጥበብ የሚያሳይ ነው፤ የሰዎች ጥበብ ለዚህ ምንም አስተዋጽኦ አላደረገም።
-
-
‘ወፎችን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ’ንቁ!—2014 | ነሐሴ
-
-
a ሰጎን በምድር ላይ ካሉት የወፍ ዝርያዎች ሁሉ ትልቋ ስትሆን በጣም ፈጣን ሯጭ ናት፤ በሰዓት 72 ኪሎ ሜትር ገደማ መሮጥ ትችላለች።
-