-
ይሖዋ ከሥቃዩ ገላገለውበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
ከዚህ አንጻር ይሖዋ እነዚህ ሰዎች ብዙ ወጪ የሚያስወጣ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ መጠየቁ የሚያስገርም አይደለም። ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች እንዲያቀርቡ አዟቸዋል፤ ይህ ደግሞ ከፍተኛ ዋጋ ያለው መሥዋዕት ነበር፤ ምክንያቱም ከጊዜ በኋላ የወጣው የሙሴ ሕግ ሊቀ ካህናቱ መላው ብሔር በደለኛ እንዲሆን የሚያደርግ ኃጢአት ቢሠራ አንድ ኮርማ መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ ያዝዝ ነበር። (ዘሌዋውያን 4:3) በሙሴ ሕግ ሥር መሥዋዕት ሆነው ከሚቀርቡት እንስሳት መካከል ብዙ ወጪ የሚያስወጣው ኮርማ ነው። ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ ይሖዋ የኢዮብ ከሳሾች የሚያቀርቡትን መሥዋዕት ለመቀበል ፈቃደኛ የሚሆነው በመጀመሪያ ኢዮብ ለእነሱ ከጸለየ እንደሆነ ገልጿል።d (ኢዮብ 42:8) ኢዮብ አምላኩ እሱን ደግፎ ሲናገር መስማቱና የይሖዋ ፍትሕ ሲያሸንፍ ማየቱ ምንኛ አስደስቶት ይሆን!
“አገልጋዬ ኢዮብም ለእናንተ ይጸልያል።”—ኢዮብ 42:8
-
-
ይሖዋ ከሥቃዩ ገላገለውበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
d ኢዮብ ሚስቱን ወክሎ እንዲህ ያለ መሥዋዕት እንዲያቀርብ እንደተጠየቀ ዘገባው አይገልጽም።
-