የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢዮብ ንጹህ አቋሙን በመጠበቁ ወሮታ ተከፍሎታል
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ግንቦት 1
    • በመጀመሪያ ይሖዋ ኤልፋዝን በልዳዶስንና ሶፋርን ገሰጻቸው። ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው ከሁሉ በእድሜ የሚበልጠውን ኤልፋዝን ይሖዋ እንዲህ ብሎታል:- “እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቁጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዶአል። አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፣ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፤ ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል።” (ኢዮብ 42:​7, 8) ይህ ምን ሊያመለክት እንደሚችል እስቲ አስብ!

      ይሖዋ የሠሩትን ኃጢያት ክብደት ለመግለጽ ኤልፋዝ፣ በልዳዶስና ሶፋር ከፍ ያለ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ፈለገ። ኤልፋዝ፣ በልዳዶስና ሶፋር ሆን ብለውም ይሁን ሳያውቁ አምላክ ‘በአገልጋዮቹ አይታመንም’ እንዲሁም ኢዮብ ጻድቅ ሆነም አልሆነ ለይሖዋ ምንም ለውጥ አያመጣም በማለት አምላክን ተሳድበዋል። እንዲያውም ኢዮብ በአምላክ ዓይን ከብል የማይበልጥ ተደርጎ እንደሚታይ ኤልፋዝ ተናግሯል! (ኢዮብ 4:​18, 19፤ 22:​2, 3) ስለዚህ ይሖዋ “ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና” ብሎ መናገሩ አይገርምም!

      ይሁን እንጂ ይህ ብቻ አይደለም። ኤልፋዝ፣ በልዳዶስና ሶፋር ኢዮብ ይህ ሁሉ ችግር የደረሰበት በራሱ ጥፋት እንደሆነ በመናገራቸው ኃጢያት ሠርተዋል። ይህ መሠረተ ቢስ ክስና ፍጹም አሳቢነት የጎደለው ንግግር ኢዮብን እንዲማረርና እንዲያዝን ከማድረጉም በላይ “ነፍሴን የምትነዘንዙ፣ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው?” በማለት በሐዘን እንዲያንጎራጉር አድርጎታል። (ኢዮብ 10:​1፤ 19:​2) እነዚህ ሦስት ሰዎች ለኃጢአታቸው መሥዋዕት እንዲያቀርብላቸው ወደ ኢዮብ ሲመጡ ምን ዓይነት ኀፍረት እንደተሰማቸው መገመት ትችላለህ!

      ይሁን እንጂ ኢዮብ የእነሱ በኀፍረት መሸማቀቅ አላስፈነደቀውም። እንዲያውም ኢዮብ ስለ ከሳሾቹ እንዲጸልይ ይሖዋ ጠይቆታል። ኢዮብ እንደተባለው በማድረጉ ተባርኳል። በመጀመሪያ ይሖዋ ኢዮብን ከያዘው ዘግናኝ በሽታ እንዲፈወስ አደረገ። ከዚያም ወንድሞቹ፣ እህቶቹና ቀድሞ የሚያውቁት ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ በተጨማሪም “እያንዳንዳቸውም የገንዘብና የወርቅ ቀለበት ስጦታ አደረጉለት።”a ከዚህም በላይ ኢዮብ “አሥራ አራት ሺህም በጎች፣ ስድስት ሺህም ግመሎች፣ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፣ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩት።”b አንዲሁም የኢዮብ ሚስት እንደተታረቀችው ማስረጃዎች ያሳያሉ። በጊዜው ኢዮብ ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች በመውለድ ሲባረክ የልጅ ልጆቹን እስከ አራት ትውልድ ድረስ አይቷል።​—⁠ኢዮብ 42:​10-​17

  • ኢዮብ ንጹህ አቋሙን በመጠበቁ ወሮታ ተከፍሎታል
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ግንቦት 1
    • ኢዮብ እሱን በመቃወም ኃጢያት ለሠሩት አጽናኞች እንዲጸልይላቸው ይሖዋ የጠየቀው ገና ጤንነቱ ሳይመለስለት በፊት ነው። ይህ ለእኛ እንዴት ያለ ግሩም ምሳሌ ነው! ይሖዋ ኃጢያታችንን ይቅር እንዲልልን እኛ በቅድሚያ የበደሉንን ይቅር እንድንል ይጠብቅብናል። (ማቴዎስ 6:​12፤ ኤፌሶን 4:​32) ሌሎች ሰዎችን ይቅር ለማለት የሚያስችል በቂ ምክንያት እያለ ፈቃደኛ ካልሆንን ይሖዋ ለእኛ ምሕረት እንዲያሳይ ልንጠብቅ እንችላለንን?​—⁠ማቴዎስ 18:​21-​35

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ