-
“የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ”መጠበቂያ ግንብ—2011 | መጋቢት 1
-
-
እስቲ ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። ጠንካራ እምነት የነበረው ኢዮብ ቁሳዊ ንብረቱን ያጣና የሚወዳቸውን ልጆቹን በሙሉ በሞት የተነጠቀ ሲሆን በአሰቃቂ በሽታም ተሠቃይቷል፤ ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ከባድ መከራዎችም ደርሰውበታል። ይህ ነው በማይባል መከራ ውስጥ ተዘፍቆ ሳለ “በሲኦል [የሰው ልጆች የጋራ መቃብር] ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ!” በማለት ወደ አምላክ ጮዃል። (ቁጥር 13 የ1954 ትርጉም) ኢዮብ ሲኦልን ከሥቃይ እፎይታ እንደሚገኝበት ቦታ አድርጎ ተመልክቶታል። በዚያ ከአስቸጋሪ ሁኔታዎችና ከሥቃይ ስለሚገላገል ልክ አምላክ እንደሸሸገው ውድ ሀብት ይሆናል።a
ታዲያ ኢዮብ ለዘላለም በሲኦል ይኖራል ማለት ነው? ኢዮብ እንዲህ የሚል እምነት አልነበረውም። ጸሎቱን ሲቀጥል “ምነው ቀጠሮ ሰጥተህ፣ ከዚያ በኋላ ባስታወስኸኝ!” ብሏል። ኢዮብ በሲኦል የሚቆየው ለጊዜው እንደሆነና ይሖዋም እንደማይረሳው ጠንካራ ተስፋ ነበረው። ኢዮብ ሳይወድ በግድ በሲኦል የሚቆይበትን ይህን ዘመን “ከግዳጅ አገልግሎት” ጋር አመሳስሎታል። ታዲያ በሲኦል የሚቆየው ለምን ያህል ጊዜ ነው? ኢዮብ “እፎይታ የማገኝበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ” በማለት ተናግሯል። (ቁጥር 14 NW) እፎይታ ማግኘት ከሲኦል መውጣትን በሌላ አባባል ከሞት መነሳትን ያመለክታል።
-
-
“የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ”መጠበቂያ ግንብ—2011 | መጋቢት 1
-
-
a አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ ‘ሰውረኝ’ የሚለው ቃል “እንደ ውድ ንብረት በአስተማማኝ ቦታ አስቀምጠኝ” የሚል ትርጉም ሊሰጠው እንደሚችል ይናገራል። ሌላ ምንጭ ደግሞ ይህ ቃል “እንደ አንድ ውድ ሀብት ደብቀኝ” የሚል ሐሳብ እንደሚያስተላልፍ ተናግሯል።
-