-
ጻድቃን አምላክን ለዘላለም ያወድሱታልመጠበቂያ ግንብ—2009 | መጋቢት 15
-
-
11, 12. የአምላክ አገልጋዮች ቁሳዊ ሀብታቸውን ለየትኞቹ ዓላማዎች ያውሉታል?
11 የአምላክ አገልጋዮች ባጠቃላይ ይኸውም በመንፈስ የተቀባው የባሪያው ክፍልም ሆነ “እጅግ ብዙ ሕዝብ” ቁሳዊ ነገሮችን በመስጠት ለጋስ መሆናቸውን አሳይተዋል። መዝሙር 112:9 “በልግስና ለድኾች ሰጠ” ይላል። በዛሬው ጊዜ የሚገኙ እውነተኛ ክርስቲያኖች ለእምነት ባልንጀሮቻቸው ሌላው ቀርቶ በችግር ላይ ላሉ ሌሎች ሰዎችም እንኳ ቁሳዊ እርዳታ ያበረክታሉ። በተጨማሪም የተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱበት ጊዜ ቁሳዊ ሀብታቸውን ተጠቅመው ለሚደረገው የእርዳታ እንቅስቃሴ ድጋፍ ይሰጣሉ። ኢየሱስ እንደተናገረው እንዲህ ማድረግ ደስታ ያስገኛል።—የሐዋርያት ሥራ 20:35ንና 2 ቆሮንቶስ 9:7ን አንብብ።
12 ከዚህም ባሻገር ይህን መጽሔት በ172 ቋንቋዎች ለማተም የሚወጣውን ወጪ አስብ፤ መጽሔቱ በቋንቋቸው ከሚዘጋጅላቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአንጻራዊ ሁኔታ ድሆች ናቸው። በተጨማሪም ይህ መጽሔት መስማት ለተሳናቸው በምልክት ቋንቋ፣ ማየት ለተሳናቸው ደግሞ በብሬል እንደሚዘጋጅ መዘንጋት አይኖርብንም።
-
-
ጻድቃን አምላክን ለዘላለም ያወድሱታልመጠበቂያ ግንብ—2009 | መጋቢት 15
-
-
“በክብር ከፍ ከፍ ይላል”
17. ጻድቃን ‘በክብር ከፍ ከፍ የሚሉት’ እንዴት ነው?
17 ዲያብሎስና እሱ የሚገዛው ዓለም የሚሰነዝሩት ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ ይሖዋን በኅብረት ማወደስ ምንኛ ያስደስት ይሆን! በአምላክ ፊት የጽድቅ አቋም ይዘው የሚኖሩ ሁሉ ይህን ዘላለማዊ በረከት ያገኛሉ። ይሖዋ የጻድቃን ‘ቀንድ በክብር ከፍ ከፍ ይላል’ የሚል ተስፋ ስለሰጠ ውርደትና ሽንፈት ተከናንበው አንገታቸውን አይደፉም። (መዝ. 112:9) የይሖዋ ጻድቅ አገልጋዮች የእሱን ሉዓላዊነት የሚቃወሙ ሁሉ ለውድቀት ሲዳረጉ በሚያዩበት ጊዜ ከፍተኛ የድል አድራጊነት ስሜት ያድርባቸዋል።
-