የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በአምላክ ፊት ንጹሕ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 2. ንጹሕ ለመሆን የትኞቹን ልማዶች ልናስወግድ ይገባል?

      መጽሐፍ ቅዱስ “ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን [እንድናነጻ]” ያሳስበናል። (2 ቆሮንቶስ 7:1) በመሆኑም ሰውነታችንንም ሆነ አእምሯችንን ሊጎዳ ከሚችል ከየትኛውም ነገር እንርቃለን። አስተሳሰባችን ይሖዋን የሚያስደስት እንዲሆን ስለምንፈልግ ተገቢ ያልሆኑ ሐሳቦችን ወደ አእምሯችን ላለማስገባት እንሞክራለን። (መዝሙር 104:34) በተጨማሪም ንግግራችን ንጹሕ እንዲሆን ጥረት እናደርጋለን።—ቆላስይስ 3:8⁠ን አንብብ።

      አካላዊ ወይም ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናችንን የሚያጎድፉብን ሌሎች ነገሮች ምንድን ናቸው? ወደ ሰውነታችን የምናስገባቸው አንዳንድ ነገሮች ሰውነታችንን ሊጎዱ ይችላሉ። በመሆኑም ሲጋራ እንደማጨስ፣ ጫት እንደመቃምና ዕፆችን አላግባብ እንደመጠቀም ያሉ መጥፎ ልማዶችን እናስወግዳለን። ከእነዚህ ልማዶች መራቃችን የተሻለ ጤንነት እንዲኖረን ያደርጋል፤ በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አክብሮት እንዳለንም ያሳያል። በተጨማሪም እንደ ማስተርቤሽንa እንዲሁም የብልግና ምስሎችን እንደመመልከት ካሉ መጥፎ ልማዶች በመራቅ ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናችንን ለመጠበቅ ጥረት እናደርጋለን። (መዝሙር 119:37፤ ኤፌሶን 5:5) እንዲህ ያሉ ልማዶችን ማሸነፍ ከባድ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ይሖዋ ይረዳናል።—ኢሳይያስ 41:13⁠ን አንብብ።

  • በአምላክ ፊት ንጹሕ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 5. ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችንና ልማዶችን ለማስወገድ ትግል አድርግ

      ቆላስይስ 3:5⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • የብልግና ምስሎችን መመልከት፣ ሴክስቲንግc እንዲሁም ማስተርቤሽን በይሖዋ ዓይን ርኩስ እንደሆኑ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

      • ይሖዋ በሥነ ምግባር ንጹሕ እንድንሆን መጠበቁ ምክንያታዊ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

      መጥፎ ሐሳቦችን ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ ንጽሕናችሁን ለመጠበቅ ቆራጥ እርምጃ ውሰዱ (1:51)

      ኢየሱስ ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናችንን ለመጠበቅ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ እንዳለብን የሚያሳይ ምሳሌ ተናግሯል። ማቴዎስ 5:29, 30⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ኢየሱስ ቃል በቃል በሰውነታችን ላይ ጉዳት ማድረስ እንዳለብን መናገሩ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ማመልከቱ ነበር። አንድ ሰው ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችን ለማስወገድ ምን ዓይነት ቆራጥ እርምጃ ሊወስድ ይችላል?d

      ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችን ለማስወገድ እየታገልክ ከሆነ ይሖዋ የምታደርገውን ጥረት ከፍ አድርጎ ይመለከታል። መዝሙር 103:13, 14⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • አንድን መጥፎ ልማድ ለማሸነፍ እየታገልክ ከሆነ ይህ ጥቅስ ተስፋ እንዳትቆርጥ የሚረዳህ እንዴት ነው?

      ተስፋ አትቁረጥ!

      አንድ መጥፎ ልማድ ሲያገረሽብህ ‘ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም፤ ታዲያ ምን አታገለኝ?’ ብለህ ልታስብ ትችላለህ። ሆኖም ይህን ለማሰብ ሞክር፦ አንድ ሯጭ ተደናቅፎ ወደቀ ማለት በውድድሩ ተሸነፈ ማለት አይደለም፤ ደግሞም ሩጫውን ከመነሻው መጀመር አያስፈልገውም። በተመሳሳይም አንድ መጥፎ ልማድ አገረሸብህ ማለት በምታደርገው ትግል ተሸነፍክ ማለት አይደለም፤ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ያደረግከው ጥረትም ከንቱ ይሆናል ማለት አይደለም። አንድን መጥፎ ልማድ ለማሸነፍ በምታደርገው ትግል እንዲህ ያለ ነገር ማጋጠሙ የሚጠበቅ ነው። ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ! በይሖዋ እርዳታ ያለብህን መጥፎ ልማድ ማሸነፍ ትችላለህ።

      ውድድር ውስጥ ያለ ሰው ከወደቀበት ሲነሳ
አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ