የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አድናቆት ይኑርህ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 5. በማህፀን ውስጥ ላለ ፅንስ ሕይወት አክብሮት ይኑርህ

      ሆዷን እየደባበሰች ያለች እርጉዝ ሴት

      ዳዊት ይሖዋ በማህፀን ውስጥ ያለን ፅንስ ሕይወትና እድገት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመለከት ገልጿል። መዝሙር 139:13-17⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በይሖዋ አመለካከት የአንድ ሰው ሕይወት የሚጀምረው ሲፀነስ ነው ወይስ ሲወለድ?

      ይሖዋ ለጥንቶቹ እስራኤላውያን የሰጠው ሕግ ለእናቶችና በማህፀን ውስጥ ላሉ ልጆች ጥበቃ ያደርግ ነበር። ዘፀአት 21:22, 23, 25⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • ይሖዋ ሳያስበው በማህፀን ውስጥ ያለን ፅንስ ሕይወት ላጠፋ ሰው ምን አመለካከት አለው?

      • ሆን ብሎ እንዲህ ለሚያደርግ ሰው ምን አመለካከት የሚኖረው ይመስልሃል?b

      • አምላክ ከዚህ ጋር በተያያዘ ስላለው አመለካከት ምን ይሰማሃል?

      ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ ልክ እንደ አምላክ ለሕይወት ከፍተኛ ዋጋ መስጠት (5:00)

      ለሕይወት ከፍተኛ አክብሮት ያላት ሴትም እንኳ ውርጃ ከመፈጸም ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌላት ሊሰማት ይችላል። ኢሳይያስ 41:10⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • አንዲት ሴት ውርጃ እንድትፈጽም ጫና በሚደረግባት ጊዜ ማን ሊረዳት ይችላል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

  • በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አድናቆት ይኑርህ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • b ቀደም ሲል ውርጃ የፈጸሙ ሰዎች ከልክ ባለፈ የጥፋተኝነት ስሜት ሊዋጡ አይገባም፤ ይሖዋ ይቅር ሊላቸው ይችላል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በዚህ ምዕራፍ ውስጥ “ምርምር አድርግ” በሚለው ክፍል ሥር የተጠቀሰውን “መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ውርጃ ምን ይላል?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ