-
በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አድናቆት ይኑርህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. የይሖዋ ስጦታ ለሆነው ሕይወት አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ ለአንተ ያለውን ፍቅርና አሳቢነት ማሳየት የጀመረው በእናትህ ማህፀን ውስጥ ከተፀነስክበት ጊዜ አንስቶ ነው። የአምላክ አገልጋይ የነበረው ዳዊት “ፅንስ እያለሁ እንኳ ዓይኖችህ አዩኝ” በማለት በመንፈስ መሪነት ተናግሯል። (መዝሙር 139:16) የአንተ ሕይወት በይሖዋ ፊት በጣም ውድ ነው። (ማቴዎስ 10:29-31ን አንብብ።) የሌላን ሰው ሌላው ቀርቶ የራስን ሕይወት ሆን ብሎ ማጥፋት አምላክን በጣም ያሳዝነዋል።a (ዘፀአት 20:13) ሳያስፈልግ ሕይወታችንን አደጋ ላይ መጣላችን ወይም የሌሎችን ሕይወት ከአደጋ ለመጠበቅ ተገቢውን ጥንቃቄ አለማድረጋችንም አምላክን ያሳዝነዋል። የራሳችንን ሕይወት ከአደጋ በመጠበቅና ለሌሎች ሕይወት አክብሮት በማሳየት ግሩም ለሆነው የሕይወት ስጦታ አድናቆት እንዳለን እናሳያለን።
-
-
በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አድናቆት ይኑርህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
5. በማህፀን ውስጥ ላለ ፅንስ ሕይወት አክብሮት ይኑርህ
ዳዊት ይሖዋ በማህፀን ውስጥ ያለን ፅንስ ሕይወትና እድገት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመለከት ገልጿል። መዝሙር 139:13-17ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
በይሖዋ አመለካከት የአንድ ሰው ሕይወት የሚጀምረው ሲፀነስ ነው ወይስ ሲወለድ?
ይሖዋ ለጥንቶቹ እስራኤላውያን የሰጠው ሕግ ለእናቶችና በማህፀን ውስጥ ላሉ ልጆች ጥበቃ ያደርግ ነበር። ዘፀአት 21:22, 23, 25ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ሳያስበው በማህፀን ውስጥ ያለን ፅንስ ሕይወት ላጠፋ ሰው ምን አመለካከት አለው?
ሆን ብሎ እንዲህ ለሚያደርግ ሰው ምን አመለካከት የሚኖረው ይመስልሃል?b
አምላክ ከዚህ ጋር በተያያዘ ስላለው አመለካከት ምን ይሰማሃል?
ለሕይወት ከፍተኛ አክብሮት ያላት ሴትም እንኳ ውርጃ ከመፈጸም ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌላት ሊሰማት ይችላል። ኢሳይያስ 41:10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
አንዲት ሴት ውርጃ እንድትፈጽም ጫና በሚደረግባት ጊዜ ማን ሊረዳት ይችላል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?
-
-
በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አድናቆት ይኑርህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
b ቀደም ሲል ውርጃ የፈጸሙ ሰዎች ከልክ ባለፈ የጥፋተኝነት ስሜት ሊዋጡ አይገባም፤ ይሖዋ ይቅር ሊላቸው ይችላል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በዚህ ምዕራፍ ውስጥ “ምርምር አድርግ” በሚለው ክፍል ሥር የተጠቀሰውን “መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ውርጃ ምን ይላል?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።
-